Filtrer par genre

የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ

የኔ ታሪክ፤ ከኢትዮጵያ እስከ አውስትራሊያ

SBS

ይህ ፕሮጄክት ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የትውልድ አገራቸውን ስለምን ለቅቀው እንደወጡ፣ በተለያዩ አገራት የስደት ሕይወት ውስጥ እንደምን እንዳለፉና በታደገቻቸው ሁለተኛ አገራቸው አውስትራሊያ የዳግም ሠፈራ ሕይወት የገጠሟቸውን ተግዳሮችና የተቸሯቸውን መልካም ዕድሎች ለማንፀባረቅ ያለመ ነው። ትረካዎቹ የኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የግለሰብ ሕይወት ጉዞዎች፣ ስኬቶች፣ ትግሎች፣ አይበገሬነትና ለአውስትራሊያ መብለ-ባሕል ድርና ማግ ያበረከቷቸውን ማለፊያ አስተዋፅዖዎች አጉልቶ ለማሳየት ነው።

45 - ድምፃዊና መሰንቆኛ ደርብ ዘነበ ደሳለኝ፤ ከጎንደር እስከ አውስትራሊያ
0:00 / 0:00
1x
  • 45 - ድምፃዊና መሰንቆኛ ደርብ ዘነበ ደሳለኝ፤ ከጎንደር እስከ አውስትራሊያ

    ድምፃዊና መሰንቆ ተጫዋች ደርብ ዘነበ ደሳለኝ፤ ድምፃዊት እናቱና አኮርዲዮን ተጫዋች አባቱ እንደምን የሙዚቃ ፍቅር አሳድረውበት በአምስት ዓመቱ ማንጎራጎር እንደጀመረ ያወጋል። በሀገረ አውስትራሊያ የሙዚቃ ሕይወቱ ስለ ገጠሙት ተግዳሮቶችና መልካም ዕድሎችም ይናገራል።

    Tue, 04 Aug 2026 - 12min
  • 44 - "ተግዳሮት ፊታችን ሲጋረጥ፣ መልካም ዕድልንም ይዞ እንደሚመጣ ማመን፤ ተስፋ አለመቁረጥና ራስን ለአዲስ ነገር ክፍት ማድረግ ያስፈልጋል" በኩረ ትጉኅን ኃይለልዑል ገብረሥላሴ

    በኩረ ትጉኅን ኃይለልዑል ገብረሥላሴ፤ ከውልደትና ዕድገት፣ የትምህርትና ሥራ፣ የተግዳሮትና ስኬት የሠፈራ ሕይወታቸውን የዳሰሱበትን የግለ ሕይወት ትረካ በምልሰታዊ ምልከታ ይቋጫሉ። የወደፊት ትልማቸውንም ያጋራሉ።

    Thu, 12 Feb 2026 - 12min
  • 43 - በኩረ ትጉኅን ኃይለልዑል ገብረሥላሴ፤ ትምህርት፣ ሥራና የአውስትራሊያ ክብር ሽልማት

    በኩረ ትጉኅን ኃይለልዑል ገብረሥላሴ፤ በሀገረ አውስትራሊያ ከመንፈሳዊ የአገልግሎት ተልዕኳቸው ጎን ለጎን ስላካሔዷቸው የትምህርትና የሥራ ዓለም ሕይወታቸው ነቅሰው ያወጋሉ።

    Thu, 12 Feb 2026 - 22min
  • 42 - በኩረ ትጉኅን ኃይለልዑል ገብረሥላሴ፤ ከነገሌ ቦረና እስከ አውስትራሊያ

    በኩረ ትጉኅን ኃይለልዑል ገብረሥላሴ፤ ከውልደት ቀዬአቸው ነገሌ ቦረና እስከ ሁለተኛ ሀገራቸው አውስትራሊያ የተጓዙበትን የመንፈሳዊና ዓለማዊ ግለ ሕይወት ታሪካቸውን ያጋራሉ።

    Tue, 10 Feb 2026 - 20min
  • 41 - ሀገራዊ ቃል ኪዳን "ባለቤቴን ለትዳር ስጠይቃት 'እኔ ሀገሬ ላይ ነው መኖር የምፈልገው፤የአንቺ ሃሳብ ምንድነው? ይህን ማወቅ አለብኝ አልኳት' ዳንኤል አለማር

    ዳንኤል አለማር፤ በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅታችን የግለ ታሪክ ወጉ እንደምን በለጋ የወጣትነት ዘመኑ ከእነ ቤተሰቡ ለሀገረ ኬንያ የስደት ሕይወት እንደበቃና እንደተወጣው አውግቷል። በመቋጫው፤ የአውስትራሊ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ጅማሮውን፣ ተግዳሮቶችና መልካም ዕድሎችን አንስቶ ይናገራል።

    Sat, 30 Aug 2025 - 22min
Afficher plus d'épisodes