Nach Genre filtern

Great Truths Podcast (Amharic)

Great Truths Podcast (Amharic)

ዶ/ር ቤንጃሚን ዲን

This is the Amharic version of the Great Truths Podcast.

ይህ ፖድካስት የእግዚአብሔር ቃልን በተሻለ መንገድ ለመረዳት እና የመፅሐፍ ቅዱስን መልዕክት ዛሬ ለእኛ ምን እንደሆነ ለማወቅ ይረዳናል። ታላቅ እውነት (Great Truths) ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ ከ 10 ሚሊዮን በላይ የሆኑ የወንጌል አማኝ መሪዎችን (መጋቢዎች፣ እረኞች፣ ቄሶች፣ ሰባኪዎች፣ እና ወንጌላውያኖችን) ለማገልገል የሚፈልግ፣ ደግሞም በአለማችን ያሉ 660 ሚሊዮን ወንጌል አማኝ ክርስትያኖችን ከፍተኛ ጥራት ባላቸው የሚዲያ አማራጮች መፅሐፍ ቅዱስን ለማስተማር የሚሻ ተቋም ነው። ለበለጠ መረጃ እና የእያንዳንዱን ምዕራፍ ሙሉ መፅሐፍ ከተጨማሪ ግብዐቶች ጋር ለማግኘት ድህረ ገፃችንን ይመልከቱ https://amharic.greattruthsglobal.org/ 



35 - መላእክት #5 | መላእክት በምን ዓይነት መልክ ይገለጣሉ ወይም ይታያሉ?
0:00 / 0:00
1x
  • 35 - መላእክት #5 | መላእክት በምን ዓይነት መልክ ይገለጣሉ ወይም ይታያሉ?

    በተለምዶ መላእክት ለሰው ልጆች በሥጋ ዓይን የሚታዩ ፍጥረታት አይደሉም፡፡ በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ መላእክት በወንዶች መልክ የሚገለጡ ፍጥረታት ናቸው (ዘፍ. 18፡2፤ቁ. 16፤፤ 19፡1-22 መሳፍ. 13፡3-21፤ እብ 13፡2)፡፡ ከመለኮታዊ ሥልጣናቸው የተነሳ አንዳንዴ መላእክት የሚያስፈሩ ናቸው፡፡ በተፈጥሮ ባህሪያቸው መላእክት በሚታይ መልኩ ሲገለጡ የሚያስፈራ ሳይሆን በልዩ የእግዚአብሄር ክብርና ግርማ የተሞሉ እና በሚያስደንቅ ሁኔታም የሚገለጡ ናቸው (ዘኁ. 22፡31፤ 2 ነገስት 6፡17፤ ዳን. 10፡4-9፤ ማቴ. 28፡3፤ ሉቃ. 2፡9 እና ራእይ 10፡1-3)፡፡ በጥቂቱ ሊያስደንቀን የሚሞክረው ነገር ቢኖር ዮሃንስ ሁለት ጊዜ የእግዚአብሄርን መልእክት ወደርሱ ያመጣውን መልኣክ ሊያመልከው ወይም ሊሰግድለት ሞክሮ ነበር፡፡ ነገር ግን መልኣኩ ራሱ ይህንን ጉዳይ እንደተቃወመው እንመለ...

    Mon, 19 Jan 2026
  • 34 - መላእክት #6 | መላእክት በምድር ላይ ዋናው ተግባራቸው ምን ይመስላል?

    በምድር ላይ የመላእክት ዋናው ሥራቸው ወይም ተግባራቸው እግዚአብሄርን ማምለክና ማገልገል ነው፡፡ በሰማይ ያላቸው የተለምዶ ሥራቸውም እግዚአብሄርን ማመስገን ሲሆን በተለየና ባልተለመደ ሁኔታ ደግሞ ስናየው የእግዚአበሄርን ታሪካዊ የመዋጀትና የመታደግ ሥራውን ወደ ህዝቡ ዘንድ ማሳለጥ ነው፡፡ በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ ገና ከመጀመሪያው አካባቢ ጀምሮ የጌታ መላኣክ ወይም የእግዚአብሄር መልኣክ የሚሉ ሃሳቦች ከእግዚአብሄር ከራሱ ሥራና ተግባር ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡

    Mon, 26 Jan 2026
  • 33 - መላእክት #4 | በአጠቃላይ የአቋማቸው ሁናቴ ምን ይመስላል?

    መጽሃፍ ቅዱሳችን በግልጽ እና ያለምንም ማመንታት እንደሚነግረን መላእክት ከእግዚአብሄር በታች የሆኑ ፍጥረታትና በእርሱ እቅድና ፈቃድ ብቻ የሚመላለሱና የሚመሩ ናቸው፡፡ ስለዚህ በመላእክትና በእግዚእበሄር መሃል ያለው ልዩነት ግልጽ ነው፡ ምክኒያቱም እነርሱ የእርሱ ናቸውና (መዝ. 104-4)፡፡ እያንዳንዳቸውም በየግላቸውና በተለየ ሁኔታ በእግዚአብሄር በራሱ፤ ለእርሱም ክብር ለሚሆን አገልግሎት የተመረጡ ናቸውና (1 ጢሞ. 5፡21)፡፡ እንዲሁም እንደ እግዚአብሄር ያለ ማን ነው; የሚል ትርጉም ያለው የሚካኤል እና እግዚአብሄር ኃያል ነው የሚል ትርጉም ያለው የገብርኤል የስሞቻቸው ትርጉም በመላእክቱና በእግዚአብሄር መሃል ያለውን በምንም ዓይነት ሁኔታ የማይቆረጠውን ግንኙነት ያሳያል፡፡

    Mon, 12 Jan 2026
  • 32 - መላእክት #3 | በሰማያዊ ሥፍራ መደራጀታቸውና ልዩ ሚናቸው

    መላእክት የሚኖሩት በሰማይ ነው (ሉቃስ 2፡15)፡፡ በሰማያዊው ዙፋኑም ፊት ለፊት እግዚአብሄር የሚያዛቸውን ሁሉ ይታዘዙታል፡፡ ለእግዚአብሄር አገልግሎትና ፈቃዱንም ለማድረግ እንዲሁም እርሱን ለማመስገንና ለማምለክ ሁልጊዜ የተዘጋጁ ናቸው (መዝ. 103፡2021)፡፡ የእግዚአብሄርንም ፊት እያዩ ያመልኩታል (ማቴ 18፡10)፡፡ በአጭሩ ሲገለጽ የመላእክት ሥራቸው በሰማያት ሆነው እግዚአብሄርን መታዘዝ፤ ማምለክና ማመስገን ነው፡፡

    Sun, 11 Jan 2026
  • 31 - መላእክት #2 | የተፈጥሮ ችሎታና አቅም

    መልኣክ የሚለው ቃል መጽሃፍ ቅዱስ በተጻፈባቸው በሁለቱ ቋንቋዎች የሚለውን ለመረዳት መሞከር ይጠቅመናል፡፡ በእብራይስጥ ቋንቋ (mal’ak) ማልኣክ የሚል ሲሆን በግሪክ ቋንቋ ደግሞ (angelos) አንጅሎስ ይላል፡፡ ይህም የሚያመለክተን የመላእክት ዋናው አገልግሎታቸው እና ተግባራቸው ዜና ተሸካሚዎች እና አስተላላፊዎች፤ አዋጅ ነጋሪዎችና መልእክተኞች እንደሆነ ነው፡፡

    Mon, 29 Dec 2025
Weitere Folgen anzeigen