Filtrer par genre
- 6158 - #119 Talking about hay fever (Med) - #119 Talking about hay fever (Med)
Learn English useful for talking about hay fever. Practise everyday phrases for describing symptoms, talking about medicine, and responding kindly when someone has hay fever. - ስለ ሄይ ፊቨር (hay fever) ለመናገር እንግሊዝኛን ይማሩን ይጠቀሙ። የሕመም ምልክቶችን ገላጭ ስለሆኑ አዘቦታዊ ቃለ ሐረጎች፣ ስለ መድኃኒትና በሄይ ፊቨር የታመመን ሰው በትሁት አንደበት ማናገርን ይለማመዱ።
Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here.
- ቃለ ሐረጎችን መማርን ከእዚህ ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶች ይለማመዱና የተማሩትን እዚህ
ይፈትኑ።Thu, 01 Oct 2026 - 10min - 6157 - የአውስትራሊያ መንግሥት ቬይትናም ውስጥ አንድ ለእሥር የተዳረገ ዜጋውን እንዲያስፈታ ግፊት እየተደረገበት ነው
የአውስትራሊያ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የብሔራዊ ባንክ የወለድ መጠን ጭማሪ ለመንግሥት የምጣኔ ሀብት አስተዳደሩ ላይ ለውጥ እንዲያካሂድ የማስጠንቀቂያ ደወል እንደሁ አመላከተ
#sbsaudiopodcastWed, 30 Sep 2026 - 07min - 6156 - "ኢሬቻ ለእግዚአብሔር ምስጋና የምናቀርብበት እንጂ ከሃይማኖት ጋር ግንኙነት የለውም፤ መልካም የኢሬቻ በዓል" አቶ አብደታ ሆማ
አቶ አብደታ ሆማ፤ የቪክቶሪያ ኢሬቻ በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ ፕሬዚደንት፤ የኢሬቻ ክብረ በዓል ሜልበርን አውስትራሊያ ውስጥ እንደምን መከበር እንደጀመረና ዘንድሮም እንደምን ተከብሮ እንደዋለ ይናገራሉ።
#sbsaudiopodcastWed, 30 Sep 2026 - 13min - 6155 - " 'ኢሬቻ ከጨለማ አውጥተኸን ለብርሃን ስላደረስከን እናመሰግናለን' የሚባልበት ቀን ነው" ወ/ሮ ይፍቱ ሚደቅሳ
የኢሬቻ በዓል 2026 በሜልበርን Wilson Botanic Park እሑድ መስከረም 17 / ሴፕቴምበር 27 በኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላትና ተጋባዥ እንግዶች ተከብሮ ውሏል። ከታዳሚ የማኅበረሰብ አባላት እስከ አባ መልካ የበዓሉን አከባበር አስመልክተው አተያዮቻቸውን ያጋራሉ።
#sbsaudiopodcastTue, 29 Sep 2026 - 08min - 6154 - Who really runs Australia, and where you fit in | How Australia Works - በእርግጥ አውስትራሊያን የሚያስተዳድረው ማን ነው? የእርስዎ ሥፍራስ የት ነው? | አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር
Do you know who can help you with a business permit, a rental problem or family support? Through the stories of Fedele, Carol and Abeer, learn how Australia’s three levels of government work. Find out what local, state or territory, and federal governments are responsible for and where to turn for help. - የንግድ ፈቃድ ለማግኘት፣ የቤት ኪራይ ችግርዎን ለመፍታት ወይም የቤተሰብ ድጋፍ ለማግኘት ማን ሊያግዝዎ እንደሚችል ያውቃሉን? ከፌደል፣ ካሮልና አቢር ታሪኮች የአውስትራሊያ ሶሶት የመንግሥት ደረጃዎች እንደምን እንደሚሠሩ ይረዱ። የአካባቢ፣ ክፍለ ሃገር ወይም ግዛትና የፌዴራል መንግሥታት ኃላፊነት ምን እንደሆነና ለእገዛ ወዴት ማምራት እንዳለብዎት ይወቁ።
How Australia Works is an SBS podcast that uses real stories and clear explanations to help you understand how government work in Australia, how laws are made and changed, and how you can have a say. Listen to the series and find shorter versions in 60 languages on the How Australia Works main page. - አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር የ SBS ፖድካስት አውስትራሊያ ውስጥ የአውስትራሊያ መንግሥት እንደምን እንደሚንቀሳቀስ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚለወጡ፤ እርስዎም አተያይዎን እንደምን እንደሚያጋሩ እውነተኛ ታሪኮችን በመንቀስ ግንዛቤን እንዲጨብጡ የሚያግዝዎ ነው። ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቹን ያድምጡ፤ ቅንጭብ ዝግጅቶቹንም በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ ያግኙ።Tue, 29 Sep 2026 - 08min - 6153 - You are already inside the system | How Australia Works - ከወዲሁ ሥርዓተ ስሪቱ ውስጥ ተካትተዋል | አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር
How do Australia’s governments, laws and public services affect your everyday life? Through real stories, this introduction to the series shows you where to start when you need information and support, and how to question a decision. - የአውስትራሊያ መንግሥታት፣ ሕጎችና ሕዝባዊ አገልግሎቶች እንደምን የእርስዎ የዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ ተፅዕኖ አንዳላቸው? እውነተኛ ታሪኮችን ተመርኩዞ፤ ይህ መንደርደሪያ መረጃንና ድጋፍን ሲሹ፤ ሲልም በውሳኔ ላይ ጥያቄን ለማንሳት ከተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቹ ውስጥ ከየት መነሳት እደሚችሉ አመላካች ነው።
How Australia Works is an SBS podcast that uses real stories and clear explanations to help you understand how government work in Australia, how laws are made and changed, and how you can have a say. Listen to the series and find shorter versions in 60 languages on the How Australia Works main page. - አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር የ SBS ፖድካስት አውስትራሊያ ውስጥ የአውስትራሊያ መንግሥት እንደምን እንደሚንቀሳቀስ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚለወጡ፤ እርስዎም አተያይዎን እንደምን እንደሚያጋሩ እውነተኛ ታሪኮችን በመንቀስ ግንዛቤን እንዲጨብጡ የሚያግዝዎ ነው። ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቹን ያድምጡ፤ ቅንጭብ ዝግጅቶቹንም በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ ያግኙ።Tue, 29 Sep 2026 - 04min - 6152 - የተባበሩት መንግሥትታ ድርጅት፣ የአፍሪካ ኅብረትና የውጭ ሀገር መንግሥታት በሰሜን ኢትዮጵያ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ስጋቶቻቸውን ገለጡ
በ 660 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚገነባው የኢትዮ - ጂቡቲ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ በሁለት ዓመታት ውስጥ ተጠናቅቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተገለጠ
#sbsaudiopodcastMon, 28 Sep 2026 - 12min - 6151 - የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት የበጀት ጉድለት ከተገመተው ያነሰ ሆኗል
አምስት ግለሰቦች ዩናይትድ ስቴትስ ኢራን ላይ ለጥቃት በተጠቀመችበት አንድ የእንግሊዝ አየር ኃይል ጦር ሠፈር አካባቢ በሽብር ተግባር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ
#sbsaudiopodcastMon, 28 Sep 2026 - 06min - 6150 - " እንኳን ለደመራ እና የመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ " - መላከ አርያም ቀሲስ ተስፋ ህሩይ
መላከ አርያም ቀሲስ ተስፋ ህሩይ በሜልበርን የደብረሰላም መድሃኒአለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ፤ የዘንድሮውን በአል አስመልክተው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
#sbsaudiopodcastSun, 27 Sep 2026 - 04min - 6149 - ኒውዮርክ ላይ የተከፈተው የተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ የሞቁና የከረሩ አተያዮች ገጠሙትWed, 23 Sep 2026 - 07min
- 6148 - የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ቢሮ የሥራ አጥነት ምጣኔ 9.6 በመቶ ደርሷል አለWed, 23 Sep 2026 - 10min
- 6147 - "አቀላለጠው" በድምፃዊት ዓለም ከበደMon, 20 Feb 2017 - 12min
- 6146 - " 'አተረማመሰው' ሸፈን ብሎ ስሜት እንዲሰጥ ተደርጎ ነው የተዘፈነው፤ ሙሉ በሙሉ ስለ ወሲብ አይደለም" ድምፃዊት ዓለም ከበደTue, 22 Sep 2026 - 18min
- 6145 - "እንኳን ለአዲሱ ዓመትና ብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ፤ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን፤ ዕድራችንን ተቀላቀሉ" በፐርዝ የኢትዮ - አውስትራሊያ መረዳጃ ዕድር
በፐርዝ የኢትዮ - አውስትራሊያ መረዳጃ ዕድር ሊቀመንበር አቶ መስቀሉ ደሴና ኢንጂነር ተስፋዬ ይመር በፐርዝ የኢትዮ - አውስትራሊያ መረዳጃ ዕድር ዐቃቤ ንዋይ፤ ስለ መረዳጃ ዕድሩ የምስረታ ሂደት፣ ቅዳሜ መስከረም 16 / ሴፕቴምበር 26 በጥምረት ሊያከብሯቸው ስላሰቡት የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት 2019 እና የመስቀል በዓል መሰናዶ ይናገራሉ።
#sbsaudiopodcastMon, 21 Sep 2026 - 21min - 6144 - የክልል መንግሥታት ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ እስከ ሁለት በመቶ የሚደርስ ክፍያ ሊቀርጡ ነውMon, 21 Sep 2026 - 10min
- 6143 - አውስትራሊያ ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ምክር ቤት አባልነት ይፋ የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ ጀመረች
አውስትራሊያውያን ረጅም ዕድሜና ጤናማ ሕይወትን እንደሚኖሩ - ግና የልጆቻቸው ቁጥር አነስተኛ እንደሚሆን መንግሥታዊው ትውልድ ተሻጋሪ ሪፖርት አመለከተ
#sbsaudiopodcastMon, 21 Sep 2026 - 08min - 6142 - "ልጆችን ቋንቋቸውንና ባሕላቸውን ማስተማር ሀብት ማውረስ ነው፤ ማንነታቸውንም ማሳወቅ ነው" ዶ/ር በላቸው ጨከነ
ዶ/ር በላቸው ጨከነ የAmharicLab የጋራ መሥራች፤ በቅርቡ በይፋ የአማርኛ ቋንቋ ንባብና ፅሑፍ ስለ ጀመረው የዲጂታል መማሪያ ድረ-ገፅ አጠቃቀምና አስተምህሮት ያስረዳሉ።
#sbsaudiopodcastThu, 17 Sep 2026 - 21min - 6141 - የዓለም ባንክ 'ከ90 በመቶ በላይ የኢትዮጵያ የሕክምና ተማሪዎች በሚያገኙት ስልጠና ደስተኛ አይደሉም' አለWed, 16 Sep 2026 - 07min
- 6140 - የንግድ ተቋማት የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት የእራሱን የኢሚግሬሽን ፖሊሲ ይፋ እንዲያደርግና የዋን ኔሽን ፖሊሲ ለምጣኔ ሃብት ድቅቀት እንደሚዳርግ አሳሰቡ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋዛ ውስጥ ከፍርስራሾች ስር ተቀብረው የተገኙ አስከሬኖች ምናልባትም በዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት ሊያስፈርጁ እንደሚችል አመላከተ
#sbsaudiopodcastWed, 16 Sep 2026 - 05min - 6139 - "አውስትራሊያውያን የጎዳና ተዳዳሪዎችን እየረዳን ነው፤ አግዙን፣ተባበሩን። መልካም አዲስ ዓመት!" ወ/ሮ አዳነች ገብረማሪያምና ወ/ሮ ዘነበች በፈቃዱ
ወ/ሮ አዳነች ገብረማርያም የKulture Bridge መሥራችና ሊቀመንበር እና ወ/ሮ ዘነበች በቀለ የ Kulture Bridge መሥራችና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፤ ድርጅታቸው ለአውስትራሊያውያን የጎዳና ተዳዳሪዎች እያበረከተ ስላለው የበጎ አድራጎት ሥራዎች ይናገራሉ። መስከረም 16 / ሴፕቴምበር 26 ቅዳሜ በ153 Rainbow St, Sandgate ባሰናዱት የኢትዮጵያ 2019 አዲስ ዓመት ልዩ ዝግጅት ላይም የብሪስበንና አካባቢዋ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች አፍሪካውያውያን - አውስትራሊያውያንም በሥፍራው እንዲታደሙ ይጋብዛሉ።
#sbsaudiopodcastWed, 16 Sep 2026 - 09min - 6138 - "አዲሱን ዓመት በፍቅርና በአንድነት እንድናከብር እንጋብዛችኋለን" ወ/ት ገነት ማስረሻ
ወ/ት ገነት ማስረሻ በቪቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ምክትል ፕሬዚደንት፤ ቅዳሜ መስከረም 9 / September 19 በ Kensington Town Hall, 30-34 Bellair St, Kensington በማኅበሩ አስተናጋጅነት ስለሚከበረው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት 2019 ልዩ የበዓል ዝግጅት ፕሮግራም ያስረዳሉ።
#sbsaudiopodcastTue, 15 Sep 2026 - 04min - 6137 - የአንድ አውስትራሊያዊ አባትና ሁለት ሕፃናት ልጆች ሕይወት ባሊ - ኢንዶኔዥያ ውስጥ አለፈMon, 14 Sep 2026 - 06min
- 6136 - "አዲሱ ዓመት የጤና፣ የመተሰሳብና የፍቅር እንዲሆንልን፤ ሰላምንም ይዞ እንዲመጣልን ጥልቅ ምኞታችንን እንገልጣለን" በፐርዝ የኢትዮ- አውስትራሊያ መረዳጃ ዕድር
አቶ ብሩክ የማ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያን የመረዳጃ ዕድር ፀሐፊ፤ ስለ ዕድሩ አመሠራረትና ተልዕኮ ያስተዋውቃሉ። የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውንም በዕድሩ ስም ያስተላልፋሉ።
#sbsaudiopodcastMon, 14 Sep 2026 - 03min - 6135 - "አዲሱ አመት የታሰሩት የሚፈቱበት የተፈናቀሉት ወደቤታቸው የሚመለሱበት የወደቁት የሚነሱበት ፍቅር እና አንድነት የሚሰፍንበት የበረከት አመት ይሁንልን ።" መላክ ጸሃይ ቀሰስ መንግስቱ ሀይሌ
እንኳን 2019 የኢትዮጵያውያን አዲስ አመት አደረሰን መላክ ጸሃይ መንግስቱ ሀይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ የምስራቅ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ አህጉረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ እንዲሁም የብሪዝበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ
#sbsaudiopodcastFri, 11 Sep 2026 - 06min - 6134 - የዘንድሮው አዲስ አመት አይኖቻችንን ዘለአለማዊ ተስፋ ወደሚሆነው እግዚአብሄር የምናነሳበት ፤ ተስፋ የቆረጡ በአዲስ ተስፋ የሚታደሱበት ፤ እርሱን የሚፈልጉት ሁሉ የሚያሻቸውን የሚያገኙበት ይሁንልን ። ” ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ
የዘንድሮው አዲስ አመት አይኖቻችንን ዘለአለማዊ ተስፋ ወደሚሆነው እግዚአብሄር የምናነሳበት ፤ ተስፋ የቆረጡ በአዲስ ተስፋ የሚታደሱበት ፤ እርሱን የሚፈልጉት ሁሉ የሚያሻቸውን የሚያገኙበት ይሁንልን ። ” ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ በዘጸአት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፓስተር
#sbsaudiopodcastFri, 11 Sep 2026 - 05min - 6133 - " አዲሱ አመት አዲስ ነገርን ፤ ፍቅርን ፤ መቻቻልን ፤ ጤናን እና ሰዎች የተመኙትን የሚያገኙበት ይሁንልን "- ሼክ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር
አዲሱ አመት አዲስ ነገርን ፤ ፍቅርን ፤ መቻቻልን ፤ ጤናን እና ሰዎች የተመኙትን የሚያገኙበት ይሁንልን ሲሉ ሼክ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር በአውስትራሊያ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሪ መለክታቸውን አስተላልፈዋል ::
#sbsaudiopodcastThu, 10 Sep 2026 - 02min - 6132 - "መልካም የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት - ዕንቁጣጣሽ!" የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ እና የተቀዋሚ ቡድን መሪ አንገስ ቴይለር
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ እና የተቃዋሚ ቡድን መሪ አንገስ ቴይለር ለኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያንና ኢትዮጵያውያን የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ያቀርባሉ።
#sbsaudiopodcastThu, 10 Sep 2026 - 05min - 6131 - አዲስ ኮከብ - ድምፃዊ ጴጥሮስ ማስረሻ
በአዲስ አንፀባራቂ ኮከብነት ስሙ እየተነሳ ያለው ድምፃዊ ጴጥሮስ ማስረሻ፤ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ከጋይንት ንፋስ መውጫ እስከ ፋና ላምሮት አይዶል አሸናፊነት እንደምን እንደበቃ ያወጋል። በ2019 አዳዲስ ዘፈኖቹን በአልበም አካትቶ ለኢትዮጵያውያን እነሆኝ ለማለት መሰናዳቱንም ያበሥራል።
#sbsaudiopodcastThu, 10 Sep 2026 - 27min - 6130 - "2019 ተስፋን ይዞ፣ የደከምንበት የሚያፈራበት፣ ሐዘናችን በደስታ የሚቀየርበት፣ መከፋታችን በፈገግታ የሚተካበት ዓመት እንዲሆንልን ምኞቴ ነው" ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ
ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ - የኩዊንስላንድ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፀሐፊ፤ የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት።
#sbsaudiopodcastWed, 09 Sep 2026 - 04min - 6129 - የሃይማኖት አባቶች የ2019 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት መልዕክት በሜልበርን - ፉትስክሬይ ፓርክ
የ2019 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ቅበላ የሃይማኖት መሪዎች መልዕክትና መንፈሳዊ ዝማሬዎች ቅዳሜ ነሐሴ 30 በሜልበርን - ፉትስክሬይ ፓርክ።
#sbsaudiopodcastWed, 09 Sep 2026 - 09min - 6128 - የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት የማኅበራዊ ሚዲያ ዲጂታል ደህንነት ጥበቃ ረቂቅ ሕግ በሳንሱር ተፈርጆ ትችት ተሰነዘረበትWed, 09 Sep 2026 - 06min
- 6127 - የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) 'ሠራተኞች ማኅበራትን ማደራጀታቸውና መብታቸውን መጠየቃቸውን እንደ ተቃውሞና ችግር ፈጣሪነት መታየት የለበትም' ሲል አሳሰበMon, 07 Sep 2026 - 11min
- 6126 - "የመልካም አዲስ ዓመት ምኞቴን በኤምባሲው ዲፕሎማቶችና በራሴ ስም አቀርባለሁ" አቶ ያለለት ጌታቸው - በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ተወካይ ጉዳይ ፈፃሚ
አቶ ያለለት ጌታቸው - በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ተወካይ ጉዳይ ፈፃሚ፤ በአውስትራሊያ ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ አውስትራሊያውያን የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞትና የመጪ ሥራ ዘመን አገልግሎቶችን ያስመለከተ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።
Mon, 07 Sep 2026 - 04min - 6125 - "የዘመን መቁጠሪያችን የሚያኮራ ልዩ ሀብታችን፤ የኢትዮጵያዊነት ልዩ ሥርዓታችንም ነው" ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ
ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያ ዘውድ ምክር ቤት ፕሬዚደንት፤ በሀገር ውስጥና በባሕር ማዶ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት።
Mon, 07 Sep 2026 - 03min - 6124 - "መጪው ዓመት የሀገራችን አንድነት የሚፀናበት፤ የሰዎች ማንነት የኩራታቸው ምንጭ ብቻ የሚሆንበት ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ።" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው - በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ አዲሱን 2019 የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ ሕዝባዊ በዓል ምክንያት በማድረግ መልካም ምኞታቸውን ይገልጣሉ።
Mon, 07 Sep 2026 - 02min - 6123 - "አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያ ሀገራችን ሰላምና መረጋጋትን፤ ለወገኖቻችንም ከስጋት ነፃ የሆነ ዓመት እንዲሆን በፅኑ እመኛለሁ" ዶ/ር ለገሰ ጋረደው
ዶ/ር ለገሰ ጋረደው - የደቡብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ አዲሱን 2019 የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ ሕዝባዊ በዓል ምክንያት በማድረግ መልካም ምኞታቸውን ይገልጣሉ።
Mon, 07 Sep 2026 - 04min - 6122 - የ2019 አዲስ ዓመት ቅበላ በሜልበርን ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት አንደበት
የ2019 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ቅበላ ቅዳሜ ነሐሴ 30 በሜልበርን-ፉትስክሬይ ፓርክ በድምቀት ተከብሯል። ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የበዓሉን መሰናዶ፣ የአዲስ ዓመት ምኞትና ተስፋዎቻቸውን አሰናስለው አጋርተዋል።
Mon, 07 Sep 2026 - 16min - 6121 - የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በ "አዲስ አበባ" አዘጋጅነት በዕለተ ዕንቁጣጣሽ ሜልበርን ከተማ ላይ ደምቆ ሊከበር ነው
ወ/ሮ ነፃነት ኃይሌ እና አቶ ቶም ኑናን፤ የ New Flower Sound 2019 የኢዮሃ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ልዩ ዝግጅት አስተባባሪዎች፤ ዓርብ መስከረም 1 ቀን / September 11 በ 342 High St, Northcote ከ 6:00 pm እስከ 11:00 pm ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ታዳሚዎች ስላዘጋጁት ልዩ ኩነት ያስረዳሉ። የኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና አውስትራሊያውያን ማኅበረሰብ አባላት የአዲስ ዓመት ታዳሚ እንዲሆኑ ያጋብዛሉ።
Fri, 04 Sep 2026 - 09min - 6120 - "2019 የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ምኞቱ ዕቅዶቹ የሚሳኩበት የሰላም ዓመት ይሁንልን!" ደራሲ ታክሎ ተሾመ
የሜልበርን - አውስትራሊያ ነዋሪ፣ ደራሲ ታክሎ ተሾመ፤ መጪውን የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት አስመልክተው ለመላ ኢትዮጵያውያን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።
Thu, 03 Sep 2026 - 01min - 6119 - #118 Losing a job (Med) - #118 Losing a job (Med)
Learn English for talking about losing your job. Practise ways to explain workplace changes and sympathetic responses to someone who has had bad news. - ከሥራ መሰናበትን አስመልክተው ለመናገር እንግሊዝኛን ይማሩ። የሥራ ቦታ ለውጦችን እንዴት ማብራራት እንደሚቻል እና መጥፎ ዜና ለገጠመው ሰው ርኅራኄ የተመላበት ምላሽ አሰጣጥን ይለማመዱ።
Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here.
- ከእዚህ ክፍለ ዝግጅት ቃለ ሐረጎችን ይለማመዱ፤ የቀሰሙትንም ዕውቀት በዕንቆቅልሻችን እዚህ ይፈትኑ።Thu, 03 Sep 2026 - 10min - 6118 - በሳዑዲ አረቢያ በፍልሰተኞች መካከል በቅርቡ ከተከሰተ የቡድን ግጭትና ግድያ ጋር በተያያዘ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን ተያዙWed, 02 Sep 2026 - 08min
- 6117 - የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት በደርዘኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ኔፓል ውስጥ የደረሱበት አለመታወቅ በእጅጉ እንዳሳሰበው አስታወቀWed, 02 Sep 2026 - 05min
- 6116 - ኔፓል ውስጥ የደረሱበት አልታወቀም የተባሉ አውስትራሊያውያን ቁጥር ጨመረMon, 31 Aug 2026 - 04min
- 6115 - የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ላይ የቀረቡ ምክረ ሃሳቦችን አተገባበር የሚከታተል ገለልተኛና ሕጋዊ አካል እንዲቋቋም ጠየቀMon, 31 Aug 2026 - 10min
- 6114 - "ኢትዮጵያዊነታችንን ካላስቀደምንና በጎሳ አካሔድ የሚኬድ ከሆነ፤ አሁን እንኳ የተረፈችዋን ኢትዮጵያ ላናገኛት እንችላለን" የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ
በሕይወት ዘመናቸው ስለ "እኛና አብዮቱ" መፅሓፋቸው ሲናገሩ "ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መሆኗ ይቆጨኛል፣ ያናድደኛል፣ ያሳዝነኛል። ወደብ አልባ ሀገር ነፃ ሀገር አይደለም። መጪዎቹ የኢትዮጵያ መንግሥታት የሚያስቡበት ጉዳይ ይመስለኛል" ያሉት የቀድሞው የኢትዮጵያ ሕዝባዊት ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ ዘርፈ ብዙ አተያዮች። (ምልሰታዊ ምልከታ
Fri, 28 Aug 2026 - 28min - 6113 - "የአዲስ አበባን ሀብትና የፖለቲካ ስልጣን መቆጣጠር ኢትዮጵያን መቆጣጠር ተደርጎ በተቀናቃኝ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ቡድኖች ዘንድ በግልፅ ይታያል" ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን
ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን፤ በኦስቲን ኮሙዩኒቲ ኮሌጅ ጂ አይ ኤስ ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ ሰሞኑን "ከፑንት እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ፤ በካሳሁን ሰቦቃ በSBS የተደረጉ ቃለ መጠይቆችና መጣጥፎች" በሚል ርዕስ በዶ/ር ግርማ አውግቸው አርታኢነትና በሴማዊ ጥናቶች መካነ ተቋም አሳታሚነት ለሕትመት በበቃው መፅሐፍ ላይ "የኢትዮጵያ ታሪካዊ የመዲናዎች ዝውውር ጂኦግራፊያዊ ጠባያት" በሚል ርዕሰ መጠሪያ ስላቀረቡት የመጣጥፋቸው ጭብጦች ይናገራሉ።
Wed, 26 Aug 2026 - 14min - 6112 - 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀመረWed, 26 Aug 2026 - 09min
- 6111 - "እኔ ሀገር ያለኝ ሰው ነኝ፤ እንዴት ቢንቁኝ ነው አሜሪካን ሀገር ቀርተህ የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ሁን የሚሉኝ?" የዘመነ ቀ.ኃ.ሥ ኢትዮጵያዊ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ
ፕ/ር ዐቢይ ጣሴ፤ የማኅበራዊ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ፣ የሞሪታኒያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንትና የትምህርት ሚኒስትር አማካሪ (በወቅቱ)፤ ስለ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችና ፍልሰተኞች ሳቢና ገፊ አስባቦችን አስመልክተው በሜልበርን ዩኒቨርሲቲ ካቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ አንኳር ሃሳቦች ነቅሰው ያስረዳሉ። (ምልሰታዊ ምልከታ)
Tue, 25 Aug 2026 - 13min - 6110 - ለአንድ ወር ከስምንት ቀናት የተካሔደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ አዲስ አበባ የክርክር ምንጭ ሆናው ተጠናቅቋልMon, 24 Aug 2026 - 12min
- 6109 - በኩዊንስላንድ ብቻ ተጨማሪ 46 ሺህ የጤና ባለሙያዎችና 38 ሺህ የኮንስትራክሽን ሠራተኞች እንደሚያስፈልጉ ተመለከተMon, 24 Aug 2026 - 06min
- 6108 - #117 Borrowing books at the library (Med) - #117 Borrowing books at the library (Med)
Learn English useful for visiting a library. Practise everyday phrases for returning borrowed items, asking about late fees and due dates, renewing items, reserving titles, and using the library catalogue. - እንግሊዝኛን ይማሩ ቤተ መጽሐፍን ለመጎብኘት ይጠቅማል። የተዋሱትን ስለ መመለስ፣ ያለተከፈለ የዘገየ ክፍያንና የክፍያ ቀናትን ስለ መጠየቅ፣ የውሰት ቀናትን ማራዘም፣ በስምዎ ተመዝግቦ እንዲቆይ ማድረግንና የቤተ መፅሐፍ የይዘት ማውጫ አዘቦታዊ ቃለ ሐረጎችን ይለማመዱ።
Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here. - የዚህን ክፍለ ዝግጅታችንን ቃለ ሐረጎች ይለማመዱ፤ የተማሩትንም በዕንቆቅልሻችን እራስዎን እዚህ ይፈትኑ።Thu, 20 Aug 2026 - 14min - 6107 - በወሲባዊ ጥቃት ጥርጣሬ ሳቢያ በአምስት የሲድኒ ስዋንስ እግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ ግደባ ተጣለWed, 19 Aug 2026 - 06min
- 6106 - አዲሱ የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት በ15 ሀገሮች በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ለኢትዮጵያውያን ዜጎች መሰጠት መጀመሩን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገለጠWed, 19 Aug 2026 - 09min
- 6105 - "ለበዓለ ደብረ ታቦር እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን!" መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ጎበና
መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ጎበና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሰሜን አፍሪካ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ ስለ በዓለ ደብረ ታቦር በሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አከባበር ይገልጣሉ። መንፈሳዊ ጥሪም ያቀርባሉ።
Wed, 19 Aug 2026 - 10min - 6104 - ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ኦማን ለዩናይትድ ስቴትስና ኢራን የሰላም ስምምነት ደንቃራ ከሆነች በአሜሪካ ቦምብ ልትጋይ እንደምትችል አስጠነቀቁTue, 18 Aug 2026 - 04min
- 6103 - ‘በርካታ ሠራተኞች የጡረታ አበል ተቀማጫቸውን አስቀድመው ለቤት ብድርና ኑሮ መደጎሚያ ቢያውሉት የተሻለ ሁኔታ ላይ ይሆናሉ’ የሚለው የዋን ኔሽን ዕሳቤ ተቃውሞና ድጋፍ ገጥሞታልMon, 17 Aug 2026 - 08min
- 6102 - "ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦቻቸውን ብቻ ሳይሆን አውስትራሊያውያን ወዳጆቻቸውንም ጨምረው በአዲሱ ዓመት ዝግጅታችን ላይ እንዲገኙ እንጋብዛለን" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው ፤ በቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ቅዳሜ ሴፕቴምበር 5 / ነሐሴ 30 በፉትስክሬይ ፓርክ ከ11: 00 am እስከ 5:00 pm ስለሚከበረው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት 2019 ቅበላ መሰናዶን አስመልክተው ይናገራሉ።
Mon, 17 Aug 2026 - 22min - 6101 - በኢትዮጵያ የሚገነባው የቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ በቻይናና አሜሪካ ኩባንያዎች መካከል ከፍተኛ ጂኦፖለቲካዊና የንግድ ፉክክር ማዕከል ሆኗል ተባለMon, 17 Aug 2026 - 10min
- 6100 - የውጭ ዜጎች በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ለመግዛት ከ150 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ያላነሰ ገንዘብ እንደሚያስፈልጋቸው አዲስ መመሪያ ወጣWed, 12 Aug 2026 - 09min
- 6099 - "ግሎባላይዜሽን አሉታዊ ጎኑ ከፍ ያለ ነው፤ ብዙ የአፍሪካ ሀገሮች የተማሩ ሰዎቻቸውን በማጣት እየተራቆቱ ነው፤ የሕዝብንም ነፃነት ነጥቋል ማለት ይቻላል" ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ
የምጣኔ ሀብት ተመራማሪ ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ፤ የግሎባላይዜሽንን ታራካዊ ዳራ አጣቅሰው፣ በዘርፈ ብዙ ገፅታው እያሳደራቸው ስላሉት ምጣኔ ሀብታዊ፣ የቴክኖሎጂ፣ ሰብዓዊ መብቶች፣ የታዳጊ ሀገራት የአዕምሮ መራቆትና ያደጉ ሀገሮች የአዕምሮ ግኝት፣ የማንነት፣ ባሕላዊና ሃይማኖታዊ ተፅዕኖዎችን ነቅሰው ያስረዳሉ።
Wed, 12 Aug 2026 - 27min - 6098 - የንግድ ማኅበረሰብ አባላት የፌዴራል መንግሥቱ የኢሚግሬሽን ፖሊሲን አስመልክቶ ሁነኛ ለውጦች ከማካሔዱ በፊት በጋራ እንዲመክር ጠየቁMon, 10 Aug 2026 - 07min
- 6097 - የመሬትና ገቢዎች ተቋማትን ጨምሮ በርካታ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሆነ ማረጋገጡን የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀMon, 10 Aug 2026 - 09min
- 6096 - 2026 Census: What you need to know to ensure you’re counted - 2026 የሕዝብ ቆጠራ፤ ስለ መቆጠርዎ እርግጠኛ ለመሆን ማወቅ የሚገባዎ ምንድን ነው?
The 2026 Census is on Tuesday 11 August and every person in Australia on this night must be counted. Census data is used to understand where we live, the languages we use at home (including Auslan), the support we need and how Australia is changing as a nation. Being counted helps ensure your community, culture and beliefs are represented. Here’s what you need to know about completing the Census for your household. - የአውስትራሊያ 2026 ሕዝብ ቆጠራ ማክሰኞ ኦገስት 11 / ነሐሴ 5 ይከወናል። በዕለተ ምሽቱ ማንኛውም አውስትራሊያ ውስጥ ያለ ሰው በሙሉ የግድ ሊቆጠር ይገባል። የሕዝብ ቆጠራ ዳታ የት እንደምንኖር፣ ቤት ውስጥ የምንናገራቸው ቋንቋዎች ምን እንደሆኑ፣ ድጋፍ ለማድረግና አውስትራሊያ እንደ ሀገር እንደምን በመለወጥ ላይ እንዳለች ለመገንዘብ ይረዳል። መቆጠርዎ ማኅበረሰብዎ፣ ባሕልና እምነቶችዎ ውክልናን ስለማግኘታቸው ለማረጋገጥ ያግዛል። የቤትዎ ነዋሪዎች የሕዝብ ቆጠራን ሞልተው ስለማጠናቀቃቸው ማወቅ ግድ የሚልዎትን እነሆን።
Fri, 07 Aug 2026 - 10min - 6095 - #116 Visiting a vet (Med) - #116 Visiting a vet (Med)
Learn English useful for talking about your sick pet. Practise everyday phrases for explaining when an animal is not eating, drinking, or acting normally. - እንግሊዝኛ ይማሩ ስለ ታመመ የቤት እንሰሳዎ ለመናገር ጠቀሜታ አለው። እንሰሳት በማይመገቡበት፣ በማይጠጡበትና እንደ አዘቦታቸው በማይሆኑበት ወቅት ያንን ለመግለፅ ገላጭ ቃለ ሐረጎችን በየዕለቱ ይለማመዱ።
Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here.
- ከእዚህ ክፍለ ዝግጅት የቀሰሟቸውን ቃለ ሐረጎችን ይለማመዱና እራስዎን እዚህ በዕንቆቅልሻችን ይፈትኑ።Thu, 06 Aug 2026 - 13min - 6094 - ጋዛ ውስጥ በእሥራኤል ጥቃት ለተገደሉ ከመቶ በላይ ፍልስጥኤማውያን የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈፀመWed, 05 Aug 2026 - 07min
- 6093 - ከኢትዮጵያ ፈጣን የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ጋር ተመጣጣኝ አዲስ የሥራ ዕድል በበቂ ሁኔታ አለመፈጠሩ ለወጣቶች ከፍተኛ የሥራ አጥነት ጫና እየፈጠረ መሆኑ ተመለከተWed, 05 Aug 2026 - 07min
- 6092 - የሕዝብ ቆጠራ 2026፤ ዕለተ ቀኑ መቼ ነው? ተቆጣሪዎች እነማን ናቸው? ፋይዳውስ ምንድን ነው?
የአውስትራሊያ ሕዝብ ቆጠራ 2026 ማክሰኞ ኦገስት 11 ምሽት ይካሔዳል። ቆጠራው አውስትራሊያውያንን ብቻ ለይቶ የሚቆጥር ሳይሆን፤ ለጉብኝት አውስትራሊያ ውስጥ የሚገኙትን፣ ዓለም አቀፍ ተማሪዎችንና በጊዜያዊ ቪዛ ያሉትን ሁሉ አካታች ነው።
Tue, 04 Aug 2026 - 03min - 6091 - ድምፃዊና መሰንቆኛ ደርብ ዘነበ ደሳለኝ፤ ከጎንደር እስከ አውስትራሊያ
ድምፃዊና መሰንቆ ተጫዋች ደርብ ዘነበ ደሳለኝ፤ ድምፃዊት እናቱና አኮርዲዮን ተጫዋች አባቱ እንደምን የሙዚቃ ፍቅር አሳድረውበት በአምስት ዓመቱ ማንጎራጎር እንደጀመረ ያወጋል። በሀገረ አውስትራሊያ የሙዚቃ ሕይወቱ ስለ ገጠሙት ተግዳሮቶችና መልካም ዕድሎችም ይናገራል።
Tue, 04 Aug 2026 - 12min - 6090 - በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የራስ ገዝነት መብት የመዋቅር ማስተካከያ ሳቢያ ከ500 በላይ የአስተዳደር ሠራተኞችና 50 መምህራን ያለ ምደባ መቅረታቸው ተመለከተMon, 03 Aug 2026 - 10min
- 6089 - How to answer the 2026 Census English proficiency question | Bonus episode - የ2026 የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ጥያቄን እንደምን መመለስ እንዳለብዎ
How do you choose between "not well", "well" and "very well" when the Census asks about your English? Honorary Professor Lynda Yates explains what these answers mean in everyday life, why perfect grammar isn't the goal, and how to assess your English with confidence. - በሕዝብ ቆጠራ ወቅት ስለ እንግሊዝኛ ክህሎትዎ ሲጠየቁ "አነስተኛ"፣ "ጥሩ" እና "በጣም ጥሩ" ብለው የሚመርጡት እንደምን ነው? የክብር ፕሮፌሰር ሊንዳ ዬትስ፤ እኒህ ጥያቄዎች በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ምን ማለት እንደሆኑ፣ ስሉጥ ሰዋሰው ስለምን ግብ እንዳልሆነና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታዎን እንደምን በራስው ተማምነው እንደሚመዝኑ ያስረዳሉ።
Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here.
- የእዚህን ክፍለ ዝግጅት ቃለ ሐረጎች ይለማመዱና የተማሩትን በዕንቆቅልሻችን እዚህ ይሞክሩት።Fri, 31 Jul 2026 - 11min - 6088 - #113 Talking about winter comfort food (Med) - #113 Talking about winter comfort food (Med)
Learn English useful for talking about cosy meals and winter comfort food. Practise everyday phrases for describing cravings, warm meals, and food that makes you feel comfortable in cold weather. - እንግሊዝኛን ይማሩ - ስለ ክረምት ሙቀት ሰጪ ምቹ ምግቦች ለመናገር ጠቀሜታ አለው። መሻትን፣ አሟቂ ምግቦችንና በብርዳማ አየር ንብረት ምቾት የሚሰጥዎትን ምግብ ለመግለጥ ፍሬ ቃሎችን በየዕለቱ ይለማመዱ።
Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here.
- በእዚህ ክፍለ ዝግጅት ቃለ ፍሬዎችን መለማመዱን ይቀጥሉበት። የቀሰሙትን ዕውቅትዎንም በዕንቆቅልሻችን እዚህይፈትኑት።Thu, 30 Jul 2026 - 08min - 6087 - የዋጋ ግሽበት በቁጥጥር ስር አለመዋሉን የፌዴራል መንግሥቱ ገለጠWed, 29 Jul 2026 - 05min
- 6086 - ፕሪሚየር ጃሲንታ አለን ኃላፊነታቸውን ለቀቁ፤ ለምክትል ፕሪሚየር ኃላፊነት ሁለት ዕጩዎች ፉክክር ላይ ናቸውTue, 28 Jul 2026 - 04min
- 6085 - #115 Working on the side (Med) - #115 Working on the side (Med)
Learn English useful for talking about side hustles and earning extra income. Practise everyday phrases for describing additional work, managing responsibilities, and talking about money. - እንግሊዝኛን ይማሩ - የጎንዮሽ ሥራን ሠርቶ ተጨማሪ ገቢን ለማግኘት ጠቀሜታ አለው። ተጨማሪ ሥራን፣ ኃላፊነትን መወጣትንና ገንዘብን አስመልክቶ ለመግለፅ አዘቦታዊ ፍሬ ቃሎችን ይለማመዱ።
Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here.
- ከእዚህ ተከታታይ ክፍለ ዝግጅት ፍሬ ቃሎችን ይለማመዱ፤ እንዲሁም የተማሩት በዕንቆቅልሻችን እዚህይፈትኑ።Mon, 27 Jul 2026 - 10min - 6084 - የቪክቶሪያ ፕሪሚየር ጃሲንታ አላን በፈቃዳቸው ኃላፊነታቸውን እንደማይለቁ አስታወቁ፤ ምክትላቸው በተቀናቃኝነት ቀረቡMon, 27 Jul 2026 - 07min
- 6083 - በዓለም ባንክ የካርቦን ልቅቀት ቅነሳ ፕሮግራም ከልቅቀት የቀነሰችው ካርቦን ለሽያጭ በማቅረብ ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሀገር ሆነች
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት በቦረና ወረዳ፣ በግዮን አባይ ገዳመ አስቄጥስ ቅድስት አርሴማ፣ አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች አንድነት ገዳም ላይ በደረሰው ጥቃት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገለጡ
Mon, 27 Jul 2026 - 12min - 6082 - አውስትራሊያ ቻይና በደቡብ ቻይና ባሕር ላይ የምትከውናቸው እርምጃዎች “ስጋትን ፈጣሪና አደገኛ ድርጊትም ነው” አለችWed, 22 Jul 2026 - 04min
- 6081 - ከ100 በላይ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት በምክክር ጉባኤው ላይ በመሳተፍ ላይ እንዳሉ ተመለከተWed, 22 Jul 2026 - 07min
- 6080 - "ተመራጮች በኢትዮጵያዊነት የሚኮሩ፣ክህሎት ያላቸውና ሁሉንም በሰብዓዊነት የሚመለከቱ ከሆነ ተዓምር ይሠራል፤ ኢትዮጵያዊነታችንን ልንክድ አንችልም" አቶ ንብረት ዓለሙ
አቶ ንብረት ዓለሙ፤ የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበር ዐቃቤ ንዋይ፤ የሥራ ዘመኑ ሊጠናቀቅ የተቃረበውን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተተኪዎችን ለማስመረጥ ስለ ተመረጠው አስመራጭ ኮሚቴ ተግባራትና ተልዕኮ ያስረዳሉ።
Wed, 22 Jul 2026 - 20min - 6079 - ላ ሮሃ - ስፔይን የፊፋ 2026 የዓለም ዋንጫን አነሳች
ከ104 ፍልሚያዎችና የአንድ ወር አይረሴ የእግር ኳስ ትዝታዎች በኋላ ስፔይን የፊፋ ዓለም ዋንጫ ባለቤት ሆናለች። የ2026 ሻምፒዮናዋ ልብ ሰቃይ ፍልሚያን አካሂዳ የእግር ኳስ ዓለም ድንቅና ብርቁን ዋንጫ ከፍ አድርጋ ለማንሳት የበቃችው አርጀንቲናን 1 ለ 0 በመርታት ነው።
Mon, 20 Jul 2026 - 06min - 6078 - በኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንትነት ውድድር ለግል ድርጅቶችና ለኢንዱስትሪ መሪዎች ክፍት ተደረገMon, 20 Jul 2026 - 08min
- 6077 - ስፔይን ፈረንሳይን 2 ለ ባዶ ረትታ ለዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ደረሰች
ስፔይን ለፊፋ የዓለም ዋንጫ ውድድር ፍፃሜ ለመድረስ በጨዋታ የበላይነት ጭምር ፈረንሳይን 2 ለ 0 ድል ነስታ የ2026 የዓለም ዋንጫ ባለቤት ለመሆን የአንድ ግጥሚያ ፈሪ ላይ ናት።
Wed, 15 Jul 2026 - 06min - 6076 - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2019 የበጀት ዓመት በጀት 502.27 ቢሊዮን ብር ሆኖ ፀደቀWed, 15 Jul 2026 - 08min
- 6075 - " መጽሐፉ የተለያዩ ቃለምልልሶችንና መጣጥፎችን ቢይዝም፤ የትኛውም የሕብረተሰብ ክፍል በቀላሉ አንብቦ ሊረዳው በሚችል መልክ የተዘጋጀ ነው ። "- ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ
ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ " የኢትዮጵያ ከፑንት እስከ 21ኛው ክፍል ዘመን መጀመሪያ " መጽሐፍ አርታኢ ፤ መጽሐፉ 16 የተለያዩ ቃለ ምልልሶችን እና 10 መጣጥፎችን ያካተተ ነው ብለዋል። ቃለ- ምልልሶቹ በኤስ ቢ ኤስ ራድዮ የአማርኛ ቋንቋ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ ፤ "ከዳአማት እስከ ኢሕአዲግ" በሚል ርእስ ተዘጋጅተው በጣቢያው በተከታታይ የተላለፉ ናቸው። አስሩ መጣጥፎች በተለያዩ ፀሐፊዎች ታሪክን ፤ ባሕልን ፤ ኪነ ጥበብንና ቋንቋን መሠረት አድርገው የተጻፉ መሆናቸውን ያስረዳሉ።
Tue, 14 Jul 2026 - 16min - 6074 - How to get into inclusive football in Australia - “በአውስትራሊያ ሁሉን ሊያስትፍ በሚችለው የእግር ኳስ እንዴት መሳተፍ ይቻላል? ”
It’s no exaggeration when we hear that the FIFA World Cup is bringing the world together. After all, football is known as the world’s most popular sport. But football really begins on the suburban ovals and in the local clubs, with everyday players of all ages and abilities. Here’s how you can become one of them. - የፊፋ የዓለም ዋንጫ ዓለምን በአንድ ላይ እያሰባሰበ ነው ስንል ማጋነን አይደለም። ለዚህም ምክንያቱ እግር ኳስ በዓለም ላይ በጣም ታዋቂው ስፖርት ተብሎ ስለሚታወቅ ነው። ይሁን እና የእግር ኳስ መነሻው በአካባቢያችን ባሉ የስፖርት ሜዳዎች (suburban ovals) እና በአካባቢ ክለቦች ውስጥ ነው፤ ጨዋታው እድሜ እና ችሎታቸው የተለያየ የሆኑ ተጫዋቾችንም ያሳትፋል። እርስዎም ከእነዚህ ተጫዋቾች አንዱ መሆን የሚችሉበትን መንገድ እነሆ።
Mon, 13 Jul 2026 - 09min - 6073 - ፈረንሳይ፣ ስፔይን፣ አርጀንቲናና እንግሊዝ እንደምን ለዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ተቃረቡ?
ከ48 ሀገራት ብሔራዊ ቡድኖች መካከል አራት ቡድኖች ለዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ተቃርበዋል። ፈረንሳይ፣ ስፔይን፣ እንግሊዝና አርጀንቲና ዓይኖቻቸውን ዋንጫይቱ ላይ ጥለዋል።
Mon, 13 Jul 2026 - 06min - 6072 - ዩኒቨርሲቲዎች ዘረኝነትን እንዲፋለሙ ግድ የሚያሰኝ ደንብ ግብር ላይ ዋለMon, 13 Jul 2026 - 06min
- 6071 - The Torres Strait Islander Flag: Land, Sea and People - “የቶረስ ስትሬት ደሴት ነዋሪዎች ባንዲራ፡ መሬት፣ ባሕር እና ሕዝብ”
In Australia, you might see three flags flying together: the Australian National Flag, the Aboriginal Flag and the Torres Strait Islander Flag. Aboriginal peoples and Torres Strait Islander peoples are the two distinct Indigenous peoples of Australia, each with their own histories, cultures, languages and flag. For many Torres Strait Islander people, the flag is a powerful symbol of identity and belonging, whether they live on the islands, the mainland or overseas. - አውስትራሊያ ውስጥ፣ ሶስት ባንዲራዎች ሲውለበለቡ ሊያዩ ይችላሉ፡ የአውስትራሊያ ብሔራዊ ባንዲራ፣ የአቦርጂናል ባንድ እና የቶረስ ስትሬት አይላንደር ባንዲራ።የአቦርጂናል እና የቶረስ ስትሬት አይላንደር ሕዝቦች በአውስትራሊያ ሁለት የተለያዩ ነባር ሕዝቦች ናቸው፤ እያንዳንዳቸውም የራሳቸው ታሪክ፣ ባህል፣ ቋንቋ እና ባንዲራ አላቸው። ለአብዛኛዎቹ የቶረስ ስትሬት አይላንደር ሰዎች ይህ ባንዲራ ለማንነታቸው እና ለህልውናቸው ታልቅ ስፍራን የሚሰጡት ነው፡ በደሴቶች ላይ ሆነ በዋናው መሬት ወይም በውጭ ቢኖሩ ይህ የማይለወጥ ነው፡፡
Mon, 13 Jul 2026 - 06min - 6070 - ኢሰመኮ፤በቀጣዮቹ ዓመታት ግጭት፣ ሁከት፣ መፈናቀል፣ የሲቪክ ምሕዳርና የሚዲያ ነፃነት ጉዳዮች በሰብዓዊ መብቶች ትግበራ ላይ ዕንቅፋት ሊሆኑበት እንደሚችል ስጋቱን ገለጠ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከሚሰጡት የመኝታ አገልግሎት ላይ አምስት በመቶ የማዘጋጃ ቤት ታክስ እንዲያሰባስቡ ግዴታ የሚጥል ደንብ ተግባራዊ አደረገ
Mon, 13 Jul 2026 - 10min - 6069 - አርጀንቲና እና ስዊዘርላንድ ለሩብ ፍፃሜ ደረሱ
አርጀንቲና በአስደማሚ ግጥሚያ ከሽንፈት ራሷን ተከላክላ ግብፅን ድል ለመንሳት ስትበቃ፤ ስዊዘርላንድ በአንዲት ግብ ብልጫ ኮሎምቢያን በመለያ ፍፁም ቅጣት ምት ረትታለች።
Wed, 08 Jul 2026 - 05min - 6068 - " አላማችን በሀዘን ጊዜ መሰባሰብ ብቻ ሳይሆን በደስታውም ጊዜ አብሮ መቆም ነው :: " - ወ/ሮ ቅድስት ሰለሞን
ወ/ሮ ቅድስት ሰለሞን የኢትዮጵያውያን እድር መረዳጃ ማህበር ዋና ጸሀፊ ፤ እድሩ በመጪው ቅዳሜ ከነባር እና አዲስ ከሚገቡት እጩ አባላት ጋር ለመወያየት ጥሪ አድርጓል። እድሩ ላለፉት አስራ ሁለት አመታት ያከናወናቸውን ተግባራት እና የወደፊት እቅዶቹን በተመለከተ ውይይት እንደሚያደርግ ገልጸዋል ።
Tue, 07 Jul 2026 - 05min - 6067 - ኖርዊይ ብራዚልን አሰቀቀች፤ ሜክሲኮ ሕልሟ በራሷ ምድር ዕውን ሳይሆን ቀረ
ኖርዌይ ታሪካዊ በሆነ ድሏ የአምስት ጊዘ ሻምፒዮን የሆነችውን ብራዚል ረትታ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሩብ ፍፃሜ አልፋለች። ብራዚልም በፊናዋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ1990 የዓለም ዋንጫ ወዲህ ለሩብ ፍፃሜ ሳትደርስ ቀርታለች ።
Mon, 06 Jul 2026 - 04min - 6066 - ኢሰመኮ “በትግራይ ክልል ከመንግሥት መዋቅር ውጪ በሚገኝ ታጣቂ ቡድን የሚፈፀም የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ እንደ ጉልበት ብዝበዛና ጦር ወንጀል ሊቆጠር ይችላል” አለMon, 06 Jul 2026 - 12min
- 6065 - " ሜክሲኮ በደጋፊዎቿ ፊት ባደርገችው ጨዋታ ድል ቀንቷት ወደ 16ተኛ ዙር አለፈች "
የእግር ኳስ ኮከቦቹ ኤርሊንግ ሃላንድ እና ኪሊያን ምባፔ ፦ እያንዳንዳቸው ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ኖርዌይንና፤ ፈረንሳይን ወደ ቀጣዩ ዙር እንዲያልፉ አድርገዋል።
Wed, 01 Jul 2026 - 08min - 6064 - የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በዪኔስኮ አምስት ምርጥ የጉዞ መዳረሻዎች ወስጥ ተካተቱWed, 01 Jul 2026 - 07min
- 6063 - በኢትዮጵያ መረጃን የከለከለን የመንግስት ሀላፊን እስከ አምስት አመት የሚያስቀጣው አዋጅ በፓርላማ ጸደቀMon, 29 Jun 2026 - 11min
- 6062 - በዮጋንዳ ሁለት የብዙሀን መገናኛዎች በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ትእዛዝ ተዘጉMon, 29 Jun 2026 - 09min
- 6061 - ካናዳ ደቡብ አፍሪካን አሸንፋ ወደ 16 ቡድኖች ዙር የደረሰች የመጀመሪያዋ ቡድን ሆነችMon, 29 Jun 2026 - 06min
- 6060 - How do charities and individual fundraisers work in Australia? - በአውስትራሊያ የእርዳታ እና በግል የሚሰበሰብ ገንዘብ አካሄድ ምን ይመስላል?
What are the rules around raising money and charities? How can you ensure you don't get scammed? Here is what you need to know if you're donating, raising money yourself or launching an online crowdfunding appeal. - የእርዳታ ገንዘብን ስናሰባስብ ልንከተላቸው የሚገቡ ህጎች ምንድን ናቸው ? ላለመጭበርበራችን ምን ማርጋገጫ አለን ? እርዳታን መለገስ የሚፈልጉ ከሆነ ፤ ወይም አሰባሳቢ አልያም በኦንላይን በጋራ የእርዳታ ማሰባሰብን የሚያደርጉ ከሆነ ማወቅ የሚገባዎት ህጎች የሚከተሉት ናቸው ።
Sun, 28 Jun 2026 - 09min - 6059 - “ የዜማ ደራሲ ብሆንም በግጥሞች ምርጫ ላይ በጣም እጠነቀቃለሁ ። ” - ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ
ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በዜማ ደራሲንቱ ይበልጥ የሚታወቅ ሲሆን የዜማ ስራውንም አገራዊ ለሆኑ ዘፈኖች በማበርከት ይታወቃል ፤ የሙዚቃ ስራው ቤተሰብ ህይወቱን ከልጆቹ ጋር እንዲጣጥም እንደረዳው ይናገራል ።
Sun, 28 Jun 2026 - 27min
Podcasts similaires à SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
El Partidazo de COPE COPE
Herrera en COPE COPE
La Linterna COPE
Dante Gebel Live Dante Gebel
Es la Mañana de Federico esRadio
La noche de Cuesta esRadio
La Trinchera de Llamas esRadio
Hondelatte Raconte Europe 1
Affaires sensibles France Inter
LEGEND Guillaume Pley
El colegio invisible OndaCero
La Rosa de los Vientos OndaCero
Les grands dossiers de l'Histoire par Franck Ferrand Radio Classique
Espacio en blanco Radio Nacional
Enquêtes criminelles RTL
Entrez dans l'Histoire RTL
Le grand récit RTL
Les Grosses Têtes RTL
L'Heure Du Crime RTL
Parlons-nous RTL
El Larguero SER Podcast
SER Historia SER Podcast
Todo Concostrina SER Podcast
Un Libro Una Hora SER Podcast
Autres podcasts de Société et Culture
Conversations ABC Australia
Casefile True Crime Casefile Presents
Forensic Files HLN
The Diary Of A CEO with Steven Bartlett DOAC
Ukraine: The Latest The Telegraph
Unravel ABC Australia
Forbidden History Like A Shot Entertainment
Unexplained iHeartPodcasts
Barangay Love Stories Barangay LS 97.1 Manila | GMA Network Inc.
Late Night Live — Full program podcast ABC Australia
TED Talks Daily TED
Stuff You Should Know iHeartPodcasts
The Megyn Kelly Show SiriusXM
Australia All Over ABC Australia
Mamamia Out Loud Mamamia Podcasts
The Poisoned Wife The Australian
Life Uncut LiSTNR
Legends of the Old West Black Barrel Media
Papa Dudut Stories Papa Dudut | TAGM Marketing Solutions Inc.
Crime Beat Curiouscast
