Podcasts by Category
- 6202 - "ማኅበረሰባዊ ትብብር በማድረግ ልጆቻችን ከእሥር ቤት ወጥተው ተመለሰው እንዳይገቡና እዚያም እንዳይቀሩ መንገዱን መቁረጥ አለብን" ዶ/ር ብርሃን አሕመድ
ዶ/ር ብርሃን አሕመድ - የAfricause ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤ ሰሞኑን ስላቀረቡት ዓመታዊ ሪፖርትና ይፋ ስላደረጉት የመልሶ ማቋቋም ፍትሕ ፕሮግራም ፋይዳዎች ይናገራሉ።
#sbsaudiopodcastWed, 18 Nov 2026 - 10min - 6201 - የዩናይትድ ስቴትስ፣ ቻይናና ሩስያ መሪዎች በጋራ ውይይት ሊያካሂዱ ነውMon, 16 Nov 2026 - 07min
- 6200 - የዓለም ባንክ አዲስ አበባ ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት 20 በመቶውን እንደምታመነጭ ገለጠMon, 16 Nov 2026 - 08min
- 6199 - "የአዲስ አበባ ልጆች ማኅበርን ያቋቋምንበት ዓላማ 'ሳቃችን ይመለስ' በሚል ነው" ድምፃዊት ሰብለ ግርማ
የአዲስ አበባ ልጆች ማኅበር ፕሬዚደንት አቶ ወንድወሰን እሸቱ እና ድምፃዊት ሰብለ ግርማ፤ የአዲስ አበባ ልጆች ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፤ ስለ ማኅበሩ አመሠራረትና ቅዳሜ ኖቬምበር 14 / ኅዳር 5 እንደምን 10 Simme St, Sunshine West የማኅበሩን 2ኛ ዓመት በልዩ የእራት ግብዣ እንደሚያከብሩ ይናገራሉ። ለመላ የማኅበረሰብ አባላት የጥሪ ግብዣ ያቀርባሉ።
#sbsaudiopodcastThu, 12 Nov 2026 - 17min - 6198 - #123 Talking about a big night (Med) - #123 Talking about a big night (Med)
Learn everyday English for talking about a big night out, sharing or responding to gossip, and describing something that may have happened. - ስለ የምሽት መዝናኛ አወጣጥ፣ ሐሜታን ማጋራት ወይም ምላሽ ስለ መስጠትና የተከሰተን ነገር የማስረዳት አዘቦታዊ እንግሊዝኛ አነጋገር ይማሩ።
Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here. #sbsaudiopodcast - ከክፍለ ዝግጅቱ የቀሰሙትን ቃል ሐረግ ይለማመዱ። ካደመጡ በኋላ፤ ዕውቀትዎን በዕንቆቅልሻችን ይፈትሹ። #sbsaudiopodcastThu, 12 Nov 2026 - 07min - 6197 - በጦር ሜዳ የተሰው የአውስትራሊያ ወታደሮች ተዘከሩWed, 11 Nov 2026 - 06min
- 6196 - የቻይና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በኢትዮጵያና ኤርትራ የሰላምና ደኅንነት ውይይት አካሔዱWed, 11 Nov 2026 - 08min
- 6195 - አውስትራሊያ በአየር ንብረት ለውጥ ሬኮርዷ የደረሰባትን ትችት አስተባበለችMon, 09 Nov 2026 - 04min
- 6194 - የኢትዮጵያ የቡና ንግድ 878 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘቱ ተነገረMon, 09 Nov 2026 - 12min
- 6193 - "ኬር ይሁን! የዘመናት ችግሮቻችንን ነው የፈታችሁልን" የሶስት አምባ ነዋሪዎች
አቶ ዳንኤል አለማር - የጎጆ ካፌና ሬስቶራንት ባለቤት፤ ሰሞኑን በቡታጅራ (ምሥራቅ ጉራጌ) ዞን፣ ልዩ ስሙ ሶስት አምባ በየራ አካባቢ የጥርጊያ መንገድና የንፁህ ውኃ ቦኖዎች እንደምን በበጎ አድራጊ እናታቸው ወ/ሮ ዓመተማርያም አጃቦ ዳኜ አሠሪነት ተጠናቅቀው ለምረቃና ማኅበረሰባዊ አገልግሎት እንደበቁና የ312 ዓመታት ባለዕድሜ የቡየማ አንገዶ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ዕደሳ ውጥንና አዲስ የግንባታ መሠረተ ደንጊያ እንዳስጣሉ ይናገራሉ።
#sbsaudiopodcastSat, 07 Nov 2026 - 26min - 6192 - የትግራይ ክልል ባለ አደራ አስተዳደር በጦርነት የተሳተፉ ግለሰቦችን ከምርጫ የሚያግድ ደንብ አወጣWed, 04 Nov 2026 - 09min
- 6191 - "አባቴ በእዚህች ዓለም ያለችን ጊዜ ውስን ናት፤ ፍሬያማ ነገር ሠርተን እንለፍ፤ በማስተዋል እንኑር ይል ነበር" ወ/ሮ ሊዲያ ስጦታው
ወ/ሮ ሊዲያ ስጦታውና አቶ ዳንኤል ጎበና፤ በቅርቡ ከእዚህ ዓለም በዘለዓለማዊ ዕረፍት የተለዩትን ደራሲ፣ የመንፈሳዊና በጎ አድራጎት አገልጋይ አቶ ስጦታው በፍቃዱን የሕይወት ዘመን ማንነትና አንኳር አስተዋፅዖዎች አንስተው ይዘከራሉ።
#sbsaudiopodcastTue, 03 Nov 2026 - 16min - 6190 - ከተቃዋሚ ቡድኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የጋራ ብልፅግና ሀገራት መሪዎች ስብሰባ ላይ መታደም የተሰነዘረን ትችት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሌ አሉMon, 02 Nov 2026 - 07min
- 6189 - ኢትዮጵያ በአውሮፓውያኑ 2040 በከፍተኛ የሙቀት መጠን መጨመር ሳቢያ እስከ 33.3 ቢሊዮን ዶላር የጠቅላላ ሀገር ውስጥ ምርት ኪሳራ ሊገጥማት እንደሚችል ተመለከተMon, 02 Nov 2026 - 12min
- 6188 - "ምንም ማሽሞንሞን አያስፈልግም፤ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር በቪክቶሪያ ባዶ ነው፤ ደካማ ነው። ስንጓተት፤ ስንጋፋ 40 ዓመት ሞላው" አቶ በድሉ ደስታ
የኢትዮጵያውያን ማኅበር በቪክቶሪያ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ አቶ በድሉ ደስታ ስለ አመራር አባላት ምርጫ ፋይዳዎችና ሂደቶች ያስረዳሉ። የማኅበሩን የአራት አሠርት ዓመታት ድርጅታዊ ጉዞውን ነቅሰው አተያያቸውን ያንፀባርቃሉ። የአዲስ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ቅዳሜ ኅዳር 26 / ዲሴምበር 5 በ 21 Yardley St, Maidstone 2:00 pm - 5:00 pm ይካሔዳል።
#sbsaudiopodcastThu, 29 Oct 2026 - 15min - 6187 - የእሥራኤል ሀገር አቀፍ ምርጫ ውጤት ቆጠራ እየተካሔደ ነው
በኦሮሚያ ክልል በተፈጸሙ ሁለት ጥቃቶች ቢያንስ 60 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን መገደላቸውን ቅዱስ ሲኖዶሱ አስታወቀ
#sbsaudiopodcastWed, 28 Oct 2026 - 08min - 6186 - በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና ኢዜማ በአርሲ ጥቃቶች ላይ ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡና ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቁWed, 28 Oct 2026 - 08min
- 6185 - How laws change, and why it takes time | How Australia Works - ሕጎች የሚለወጡት እንደምን ነው፤ ጊዜ የሚወስዱትስ ስለምን ነው | አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር
How do laws change in Australia? Through Rodney Croome’s campaigns for human rights and marriage equality, learn how personal stories, community action, courts and parliament can help change the law, and why the process can take time. - አውስትራሊያ ውስጥ ሕጎች የሚለወጡት እንደምን ነው? በሮድኒ ክሩም የሰብዓዊ መብቶችና የጋብቻ እኩልነት የቅስቀሳ ዘመቻ አማካይነት፤ ግለ ታሪኮች፣ ማኅበረሰባዊ ድርጊቶች፣ ፍርድ ቤቶችና ፓርላማ እንደምን ሕግ እንደሚለወጥና ሂደቱም ስለምን ጊዜ ወሳጅ እንደሆነ ይረዱ።
How Australia Works is an SBS podcast that uses real stories and clear explanations to help you understand how government work in Australia, how laws are made and changed, and how you can have a say. Listen to the series and find shorter versions in 60 languages on the How Australia Works main page. - አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገበር እውነተኛ ታሪኮችን ነቅሶ፤ አውስትራሊያ ውስጥ መንግሥት እንደምን እንደሚሠራ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚሻሻሉ፣ እንደምን አተያዮን ማጋራት እንደሚችሉ ግንዛቤን የሚያስጨብጥዎ የSBS ፖድካስት ነው። ተከታትይ ክፍለ ዝግጅቶችንና አጭር ክፍለ ዝግጅቶችን በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ አግኝተው ያድምጡ።Tue, 27 Oct 2026 - 07min - 6184 - ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የተከሰቱ ሰብዓዊ ቀውሶች ተጨማሪ ግጭት ሊቀሰቅሱ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አሳሰበMon, 26 Oct 2026 - 08min
- 6183 - በደረሰባቸው ጥቃት ሳቢያ ሆስፒታል የሚገኙት የአውስትራሊያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሄለን ሄይንዝ የክብር ሞገስ ተላበሱMon, 26 Oct 2026 - 08min
- 6182 - #121 Picking up a prescription (Med) - #121 Picking up a prescription (Med)
Learn English useful for picking up prescription medicine. Practise phrases for filling a prescription, asking how to take medicine, understanding the instructions on a medicine label, and checking possible side effects and interactions with other medicines. - የሐኪም መድኃኒት ማዘዣ ለመውሰድ የሚረዱ የእንግሊዝኛ አገላለፆችን ይማሩ። የመድኃኒት ማዘዣ ለማሳከል፣ መድኃኒቱን እንዴት እንደሚወስዱ ለመጠየቅ፣ በመድኃኒት መለያ ላይ ያሉ መመሪያዎችን ለመረዳት፣ እንዲሁም ሊከሰቱ ስለሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶችና ከሌሎች መድኃኒቶች ጋር ስለሚኖሩ መስተጋብሮች ለመጠየቅ የሚጠቅሙ ቃለ ሐረጎችን ይለማመዱ።
Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here.
- ከክፍለ ዝግጅቱ የተማሯቸውን ቃለ ሐረጎች ይለማመዱ። የቀሰሙትንም እዚህ በዕንቆቅልሻችን ይፈትኑ።Thu, 22 Oct 2026 - 09min - 6181 - የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ በትግራይ፣ በአፋርና በአማራ ክልሎች የተቀሰቀሱት ግጭቶች እንዲገቱ ጥሪ አቀረቡWed, 21 Oct 2026 - 08min
- 6180 - በመንገድ እጦት ምክንት 30 በመቶ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከተቀረው ሕዝብ ጋር መገናኘት አልቻሉም ተባለWed, 21 Oct 2026 - 09min
- 6179 - #120 Going to a wedding (Med) - #120 Going to a wedding (Med)
Learn English useful for going to a wedding. Practise asking about the ceremony and reception, talking about gifts and gift registries, and inviting someone as your plus-one. - ወደ ሠርግ አካሔድን እንግሊዝኛ ይማሩ። ስለ ሥነ ሥርዓቱ፣ ግብዣ፣ ስጦታ፣ የስጦታ ምዝገባዎች እና አንድ ተጨማሪ ከጎንዎ የሚሆን ሰውን የመጋበዝ ንግግርን ይለማመዱ።
Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here.
- የክፍለ ዝግጁቱን ቃለ ሐረጎች ይለማመዱና የቀሰሙትንም በዕንቆቅልሻችን እዚህ ይፈትኑ።Tue, 20 Oct 2026 - 10min - 6178 - ዜጎች እንደምን ለውጥ ጠንሳሽ / ቀራጭ እንደሚሆኑና ድምፅዎ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው | አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር
አንድ አነስተኛ ቡድን በእርግጥ የክፍለ ከተማ ውሳኔን ማስለወጥ ይችላል? ጁሊ የማኅበረሰቧ ቤተ መጽሐፍት ሊዘጋ መሆኑን ስትሰማ፤ ከቀዬዋ ነዋሪዎች ጋር ልትታደግ ዘመቻቸውን ተቀላቀለች። ታሪኳ ፊርማዎችን በማሰባሰብ፣ የማኅበረሰብ ስብሰባዎች በመሳተፍ፣ የክፍለ ከተማ ተመራጮችን በማነጋገርና ምርጫንም በማካሔድ እንደምን በአውስትራሊያ ዲሞክራሲ ተሳታፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይቃኛል።
አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገበር እውነተኛ ታሪኮችን ነቅሶ፤ አውስትራሊያ ውስጥ መንግሥት እንደምን እንደሚሠራ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚሻሻሉ፣ እንደምን አተያዮን ማጋራት እንደሚችሉ ግንዛቤን የሚያስጨብጥዎ የSBS ፖድካስት ነው። ተከታትይ ክፍለ ዝግጅቶችንና አጭር ክፍለ ዝግጅቶችን በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ አግኝተው ያድምጡ።Tue, 20 Oct 2026 - 08min - 6177 - የፍልሰተኞች ቅነሳ ፖሊሲ አውስትራሊያን በአንድ አሠርት ዓመት ውስጥ ከአንድ ትሪሊየን ዶላር በላይ ለሆነ ጠቅላላ ብሔራዊ ዕዳ ሊዳርጋት እንደሚችል ተመለከተMon, 19 Oct 2026 - 07min
- 6176 - የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ረድኤት ማስተባበሪያ በትግራይ ክልል በርካታ ሆስፒታሎች ሥራ መጀመራቸውን አመለከተ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ድንበር ላይ ጦር መከማቸት ወደ ሰፊ ቀጣናዊ ግጭት እንዳያመራ ያላቸውን ስጋት ገለጡ
#sbsaudiopodcastMon, 19 Oct 2026 - 11min - 6175 - "ኢትዮጵያና ኤርትራ አፋሮችን ጨምረው ለ99 ዓመት የሚዘልቅ የታላቋ አሰብ ባለስልጣን በውል ሊያቋቁሙ ይገባል" አቶ ኅሩይ ተድላ ባይሩ
አቶ ኅሩይ ተድላ ባይሩ፤ የቀድሞው የኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባር (ELF) ምክትል ፕሬዚደንትና "Eritrea and Ethiopia: A front row look at issues of conflict and the potential for a peaceful resolution" መጽሐፍ ደራሲ፤ የአሰብና ሌሎችንም በኤርትራ ያሉ ሊያድጉ የሚችሉ ወደቦችንና የኢትዮጵያና ኤርትራን አሳሳቢ የጦርነት ዕሳቤ አስመልክተው ይናገራሉ። የሰላማዊ መፍትሔ ምክረ ሃሳቦቻቸውን ያጋራሉ።
#sbsaudiopodcastSat, 17 Oct 2026 - 26min - 6174 - የውይይት መድረክ፤ የአውስትራሊያ ሚና ለሰሜን ኢትዮጵያና ኢትዮ-ኤርትራ ግጭትና ውጥረት ቅነሳ
ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ (ኢትዮጵያዊት - አውስትራሊያዊት)፣ አቶ ልዑል ፍስሃ (ኢትዮጵያዊ - አውስትራሊያዊ)፣ እና አቶ ዮሐንስ ወንድማገኝ (ኤርትራዊ - አውስትራሊያዊ) የአውስትራሊያ መንግሥት ለኢትዮጵያና ኤርትራውያን አውስትራሊያውያን፤ ዐልፎም ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን በማሳደር ረገድ ለሰላም መስፈን እንደምን የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ያላቸውን ግለ አመለካከቶች ያጋራሉ።
#sbsaudiopodcastFri, 16 Oct 2026 - 13min - 6173 - የውይይት መድረክ፤ የኢትዮ-ኤርትራ ሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ ጥቅምና የወደብ አጠቃቀም
ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ (ኢትዮጵያዊት - አውስትራሊያዊት)፣ አቶ ልዑል ፍስሃ (ኢትዮጵያዊ - አውስትራሊያዊ)፣ እና አቶ ዮሐንስ ወንድማገኝ (ኤርትራዊ - አውስትራሊያዊ) የኢትዮጵያና ኤርትራን ብሔራዊ ጥቅም፣ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ማስከበርን በተመለከተ አተያዮቻቸውን ያንፀባርቃሉ።
#sbsaudiopodcastFri, 16 Oct 2026 - 18min - 6172 - የውይይት መድረክ፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያ - ኤርትራ ወታደራዊ ውጥረት ማኅበረሰባዊ የሥነ ልቦና ጫና
ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ (ኢትዮጵያዊት - አውስትራሊያዊት)፣ አቶ ልዑል ፍስሃ (ኢትዮጵያዊ - አውስትራሊያዊ)፣ እና አቶ ዮሐንስ ወንድማገኝ (ኤርትራዊ - አውስትራሊያዊ) በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ ባለው ጦርነት፤ እንዲሁም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ከርረው ያሉት ዲፕሎማሲያዊና ወታደራዊ ውጥረቶች በሀገረ አውስትራሊያ ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያውንና ኤርትራውያን፤ ትውልደ - ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የማኅበረሰብ አባላት ላይ ስላሳደራቸውና ሊያሳድሯቸው ስለሚችሉት ስነ ልቦናዊ ተፅዕኖዎች ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።
#sbsaudiopodcastThu, 15 Oct 2026 - 20min - 6171 - በርካታ አውስትራሊያውያን መንግሥት በቤት ኪራይ ክፍያ ጭማሪ ገደብ ላይ ጣልቃ ቢገባ እንደሚሹ ገለጡWed, 14 Oct 2026 - 06min
- 6170 - የተባበሩት መንግሥትታ ድርጅት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ዓለም አቀፋዊ ይዘት እንዳይኖረው ስጋት ያደረበት መሆኑን ገለጠWed, 14 Oct 2026 - 11min
- 6169 - ሕጎች እንዴት ነው የሚቀረፁት፤ እርስዎ ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩትስ እንደምን ነው | አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር
ሕጎች አውስትራሊያ ውስጥ የሚቀረፁት እንደምን ነው? በዉራንጄሪው አረጋዊ አጎት ዴቭ ዋንዲን አማካይነት የቢራራንግ እንዲሁም ያራ ወንዝ በመባል የሚታወቀውን ወንዝ ታሪክ ይቅሰሙ፤ እንደምን ፅንሰ ሃሳብ ለረቂቅ ድንጋጌነት እንደበቃ፤ በቪክቶሪያ ፓርላማ ይሁንታን እንዳገኘና ንጉሣዊ ፅድቅ ተችሮት ለሕግነት እንደበቃ።
አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገበር እውነተኛ ታሪኮችን ነቅሶ፤ አውስትራሊያ ውስጥ መንግሥት እንደምን እንደሚሠራ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚሻሻሉ፣ እንደምን አተያዮን ማጋራት እንደሚችሉ ግንዛቤን የሚያስጨብጥዎ የSBS ፖድካስት ነው። ተከታትይ ክፍለ ዝግጅቶችንና አጭር ክፍለ ዝግጅቶችን በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ አግኝተው ያድምጡ።Tue, 13 Oct 2026 - 09min - 6168 - "የተባበሩት መንግሥታት ብዙውን ጊዜ ግጭት ማስቀረት ላይ ስኬታማ ሆኖ አላየውም፤ ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ቶሎ ይገባል" ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል
ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል፤ እ.አ.አ. ከ2012-14 በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን ለአቢዪ እንዲሁም ከ2014-16 ለደቡብ ሱዳን የተመድ ፀጥታ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ዋና ኃላፊነት ሠርተዋል፤ በቅርቡም "የግጭት አዙሪት እና የአፍሪካ ቀንድ" በሚል ርዕስ መፅሐፍ ደርሰው ለአንባቢያን አበርክተዋል። ዳግም በተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያና ኤርትራን ወታደራዊ የግጭት አቅጣጫ አንስተው የሙያና የተሞክሮ ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።
#sbsaudiopodcastSun, 11 Oct 2026 - 18min - 6167 - "በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ውጊያ መቀጠሉ የሚቀር አይመስለኝም፤ በማን የበላይነትና እንዴት ይቋጫል የሚለውን ወደፊት የምናየው ነው" ሌ/ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል
ሌተና ጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል፤ እ.አ.አ. ከ2012-14 በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን ለአቢዪ እንዲሁም ከ2014-16 ለደቡብ ሱዳን የተመድ ፀጥታ ኃይል አዛዥ ሆነው ተመድበው አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ዋና ኃላፊነት ሠርተዋል፤ በቅርቡም "የግጭት አዙሪት እና የአፍሪካ ቀንድ" በሚል ርዕስ መፅሐፍ ደርሰው ለአንባቢያን አበርክተዋል። ዳግም በተቀሰቀሰው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና የኢትዮጵያና ኤርትራን ወታደራዊ የግጭት አቅጣጫ አንስተው የሙያና የተሞክሮ ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።
#sbsaudiopodcastSun, 11 Oct 2026 - 17min - 6166 - ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ አስመረቀ
ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ ያስገነባውን ሁለገብ ሕንጻ በትናንትናው እለት አስመርቋል። የደብረሰላም ሜልበርን መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን በአውስትራሊያ የመጀመሪያ እና በአባላት መጥንም ሆነ ባገልግሎት እየሰፋ በመሄዱ ፤ የአውስትራሊያና ኒውዝላንድ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት አቡነ ሉቃስ ከሀገር አሜሪካ " ርእሰ አድባራት ደብረሰላም መድሀኒአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ በአውስትራሊያ " እንዲባል ወስነዋል። መልእክታቸውም በብጹእ አቡነ ጴጥሮስ የኒውዬርክና አካባቢው ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በኩል ተላልፏል። በምረቃው ስነ ስርአት ላይ ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ የኒውዬርክና አካባቢው ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፤ ብፁዕ አቡነ ዬሴፍ የሲዳማ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ፤ በአውስትራሊያና ኒውዝላድ ያሉ የየደብሩ አስተዳዳሪዎችና ምእመናን ፤ የግብጽ ኮፕት ቤተክርስቲያን አባቶች፤ የፓርላማ አባላት ፤ ሚኒስትሮች ፤ የአካባቢው ከንቲባዎች እና ካውንስለሮች ተገኝተዋል።
#sbsaudiopodcastSun, 11 Oct 2026 - 15min - 6165 - በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የቀጥታ ጦርነት ጅማሮ ስጋት ንሯል፤ በትግራይ የጦር ኃይሎች እንቅስቃሴ ቀጥሏልFri, 09 Oct 2026 - 05min
- 6164 - "ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት በራሷ ምድር አጥቂ እንጂ ተከላካይ አልነበረችም" ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን
ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን፤ በኦስቲን ኮሙዩኒቲ ኮሌጅ ጂ አይ ኤስ ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ ሰሞኑን "ከፑንት እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ" በሚል ርዕስ በዶ/ር ግርማ አውግቸው አርታኢነትና በሴማዊ ጥናቶች መካነ ተቋም አሳታሚነት ለሕትመት በበቃው መፅሐፍ ላይ "የአድዋ ድልና ትርክት በጂኦግራፊያዊ ዕይታ ሲፈተሽ" በሚል ርዕሰ መጠሪያ ስላቀረቡት የመጣጥፋቸው ጭብጦች ይናገራሉ።
#sbsaudiopodcastWed, 07 Oct 2026 - 26min - 6163 - ኢትዮጵያ በዓባይና በቀይ ባሕር ላይ ያላትን ጥቅም ዳግም አስገነዘበች፤ በትግራይ ውጊያው ቀጥሏል
ዳግም በትረ ስልጣናቸውን የተረከቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመመስረቻ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ይፋ ንግግር፤ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት መንግሥታቸው ሁነኛ ትኩረት የሚሰጥባቸውን ዋነኛ አቅጣጫዎች አመላከቱ።
#sbsaudiopodcastTue, 06 Oct 2026 - 11min - 6162 - Why power is split, and how that protects you | How Australia Works - ስልጣን ስለምን ነው የተከፋፈለው፤ እንደምንስ ነው ለእርስዎ ጥበቃ የሚያደርገው | አውስትራሊያ እንደም እንደምትተገብር
After receiving a fine for not wearing his motorbike helmet correctly, Hugo decides to have the matter heard in court. His story explains how Parliament, government and the courts have different roles, and how some official decisions can be questioned. - የሞተር ብስክሌት ሔልሜት በአግባቡ አላደረግክም በሚል አስባብ መቀጮ ሲደርሰው፤ ሁጉ ጉዳዩ ለችሎት ስሚ እንዲቀርብለት ከውሳኔ ላይ ደረሰ። የእሱ ታሪክ ፓርላማ፣ መንግሥትና ፍርድ ቤቶች ስላሏቸው የተለያዩ ሚናዎችና እንደምን የተወሰኑ ይፋ ውሳኔዎች ጥያቄ ሊቀርብባቸው እንደሚችል ግንዛቤ ያስጨብጣል።
How Australia Works is an SBS podcast that uses real stories and clear explanations to help you understand how government work in Australia, how laws are made and changed, and how you can have a say. Listen to the series and find shorter versions in 60 languages on the How Australia Works main page. - አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር የ SBS ፖድካስት አውስትራሊያ ውስጥ የአውስትራሊያ መንግሥት እንደምን እንደሚንቀሳቀስ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚለወጡ፤ እርስዎም አተያይዎን እንደምን እንደሚያጋሩ እውነተኛ ታሪኮችን በመንቀስ ግንዛቤን እንዲጨብጡ የሚያግዝዎ ነው። ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቹን ያድምጡ፤ ቅንጭብ ዝግጅቶቹንም በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ ያግኙ።Tue, 06 Oct 2026 - 07min - 6161 - የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና አጋሮቹ መቀሌን መቆጣጠር
በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል እየበረታ ያለው ግጭት ያሳሰባት ዩናይትድ ስቴትስ ሁለቱ ሀገራት ከግጭት ተቆጥበው ወደ ንግግር እንዲመለሱ አሳሰበች
#sbsaudiopodcastMon, 05 Oct 2026 - 08min - 6160 - የአውስትራሊያ መንግሥት የከሰል ማዕድን ቁፋሮ ማስፋፋት በቅድመ COP31 ጉባኤ ተቃውሞ እየጠበቀው ነው
አውስትራሊያ ራሷን በሰከነ የምጣኔ ሃብት ሀገርነት፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ መሪነትና የታዳሽ ኃይል ማዕከልነት ለማስተዋወቅ ወጥናለች
#sbsaudiopodcastMon, 05 Oct 2026 - 05min - 6159 - የአውስትራሊያ የቋንቋ ለውጥ የአዲሱ የSBS ክለሳ ቀራጭ ይሆናል
በርካታ ከአንድ ቋንቋ በላይ ተናጋር የሆኑ ፍልሰተኛ ቤተሰቦች የSBS ሬዲዮ የተለያዩ ቋንቋ ፕሮግራሞችን ከማድመጥ የተያያዙ የግል ትዝታዎችና ልዩ ትስስሮሽ አሏቸው። እነዚህ ፕሮግራሞች ባለፉት ዓመታት ተለውጠዋል፤ ተስፋፍተዋል። እናም አሁን SBS በዘመናዊቷ አውስትራሊያ የሚታዩትን የማኅበረሰብ ለውጦችና ፍላጎቶችን ለማንፀባረቅ የቋንቋ አገልግሎቶቹን ክለሳ ለማካሄድ በመሰናዶ ላይ ይገኛል። ለክለሳውም የሕዝባዊ ምክክር ጊዜ ይኖራል። ይህም ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 3 ድረስ ይከናወናል።
#sbsaudiopodcastMon, 05 Oct 2026 - 08min - 6158 - #119 Talking about hay fever (Med) - #119 Talking about hay fever (Med)
Learn English useful for talking about hay fever. Practise everyday phrases for describing symptoms, talking about medicine, and responding kindly when someone has hay fever. - ስለ ሄይ ፊቨር (hay fever) ለመናገር እንግሊዝኛን ይማሩን ይጠቀሙ። የሕመም ምልክቶችን ገላጭ ስለሆኑ አዘቦታዊ ቃለ ሐረጎች፣ ስለ መድኃኒትና በሄይ ፊቨር የታመመን ሰው በትሁት አንደበት ማናገርን ይለማመዱ።
Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here.
- ቃለ ሐረጎችን መማርን ከእዚህ ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶች ይለማመዱና የተማሩትን እዚህ
ይፈትኑ።Thu, 01 Oct 2026 - 10min - 6157 - የአውስትራሊያ መንግሥት ቬይትናም ውስጥ አንድ ለእሥር የተዳረገ ዜጋውን እንዲያስፈታ ግፊት እየተደረገበት ነው
የአውስትራሊያ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የብሔራዊ ባንክ የወለድ መጠን ጭማሪ ለመንግሥት የምጣኔ ሀብት አስተዳደሩ ላይ ለውጥ እንዲያካሂድ የማስጠንቀቂያ ደወል እንደሁ አመላከተ
#sbsaudiopodcastWed, 30 Sep 2026 - 07min - 6156 - "ኢሬቻ ለእግዚአብሔር ምስጋና የምናቀርብበት እንጂ ከሃይማኖት ጋር ግንኙነት የለውም፤ መልካም የኢሬቻ በዓል" አቶ አብደታ ሆማ
አቶ አብደታ ሆማ፤ የቪክቶሪያ ኢሬቻ በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ ፕሬዚደንት፤ የኢሬቻ ክብረ በዓል ሜልበርን አውስትራሊያ ውስጥ እንደምን መከበር እንደጀመረና ዘንድሮም እንደምን ተከብሮ እንደዋለ ይናገራሉ።
#sbsaudiopodcastWed, 30 Sep 2026 - 13min - 6155 - " 'ኢሬቻ ከጨለማ አውጥተኸን ለብርሃን ስላደረስከን እናመሰግናለን' የሚባልበት ቀን ነው" ወ/ሮ ይፍቱ ሚደቅሳ
የኢሬቻ በዓል 2026 በሜልበርን Wilson Botanic Park እሑድ መስከረም 17 / ሴፕቴምበር 27 በኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላትና ተጋባዥ እንግዶች ተከብሮ ውሏል። ከታዳሚ የማኅበረሰብ አባላት እስከ አባ መልካ የበዓሉን አከባበር አስመልክተው አተያዮቻቸውን ያጋራሉ።
#sbsaudiopodcastTue, 29 Sep 2026 - 08min - 6154 - Who really runs Australia, and where you fit in | How Australia Works - በእርግጥ አውስትራሊያን የሚያስተዳድረው ማን ነው? የእርስዎ ሥፍራስ የት ነው? | አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር
Do you know who can help you with a business permit, a rental problem or family support? Through the stories of Fedele, Carol and Abeer, learn how Australia’s three levels of government work. Find out what local, state or territory, and federal governments are responsible for and where to turn for help. - የንግድ ፈቃድ ለማግኘት፣ የቤት ኪራይ ችግርዎን ለመፍታት ወይም የቤተሰብ ድጋፍ ለማግኘት ማን ሊያግዝዎ እንደሚችል ያውቃሉን? ከፌደል፣ ካሮልና አቢር ታሪኮች የአውስትራሊያ ሶሶት የመንግሥት ደረጃዎች እንደምን እንደሚሠሩ ይረዱ። የአካባቢ፣ ክፍለ ሃገር ወይም ግዛትና የፌዴራል መንግሥታት ኃላፊነት ምን እንደሆነና ለእገዛ ወዴት ማምራት እንዳለብዎት ይወቁ።
How Australia Works is an SBS podcast that uses real stories and clear explanations to help you understand how government work in Australia, how laws are made and changed, and how you can have a say. Listen to the series and find shorter versions in 60 languages on the How Australia Works main page. - አውስትራሊያ እንደምን እንደምትተገብር የ SBS ፖድካስት አውስትራሊያ ውስጥ የአውስትራሊያ መንግሥት እንደምን እንደሚንቀሳቀስ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚለወጡ፤ እርስዎም አተያይዎን እንደምን እንደሚያጋሩ እውነተኛ ታሪኮችን በመንቀስ ግንዛቤን እንዲጨብጡ የሚያግዝዎ ነው። ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቹን ያድምጡ፤ ቅንጭብ ዝግጅቶቹንም በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ ያግኙ።Tue, 29 Sep 2026 - 08min - 6153 - You are already inside the system | How Australia Works - ከወዲሁ ሥርዓተ ስሪቱ ውስጥ ተካትተዋል | አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር
How do Australia’s governments, laws and public services affect your everyday life? Through real stories, this introduction to the series shows you where to start when you need information and support, and how to question a decision. - የአውስትራሊያ መንግሥታት፣ ሕጎችና ሕዝባዊ አገልግሎቶች እንደምን የእርስዎ የዕለት ተዕለት ሕይወት ላይ ተፅዕኖ አንዳላቸው? እውነተኛ ታሪኮችን ተመርኩዞ፤ ይህ መንደርደሪያ መረጃንና ድጋፍን ሲሹ፤ ሲልም በውሳኔ ላይ ጥያቄን ለማንሳት ከተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቹ ውስጥ ከየት መነሳት እደሚችሉ አመላካች ነው።
How Australia Works is an SBS podcast that uses real stories and clear explanations to help you understand how government work in Australia, how laws are made and changed, and how you can have a say. Listen to the series and find shorter versions in 60 languages on the How Australia Works main page. - አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር የ SBS ፖድካስት አውስትራሊያ ውስጥ የአውስትራሊያ መንግሥት እንደምን እንደሚንቀሳቀስ፣ ሕጎች እንደምን እንደሚቀረፁና እንደሚለወጡ፤ እርስዎም አተያይዎን እንደምን እንደሚያጋሩ እውነተኛ ታሪኮችን በመንቀስ ግንዛቤን እንዲጨብጡ የሚያግዝዎ ነው። ተከታታይ ክፍለ ዝግጅቶቹን ያድምጡ፤ ቅንጭብ ዝግጅቶቹንም በ60 ቋንቋዎች አውስትራሊያ እንደምን እንደምተገብር ዋነኛ ገፅ ላይ ያግኙ።Tue, 29 Sep 2026 - 04min - 6152 - የተባበሩት መንግሥትታ ድርጅት፣ የአፍሪካ ኅብረትና የውጭ ሀገር መንግሥታት በሰሜን ኢትዮጵያ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ስጋቶቻቸውን ገለጡ
በ 660 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚገነባው የኢትዮ - ጂቡቲ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ በሁለት ዓመታት ውስጥ ተጠናቅቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ተገለጠ
#sbsaudiopodcastMon, 28 Sep 2026 - 12min - 6151 - የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት የበጀት ጉድለት ከተገመተው ያነሰ ሆኗል
አምስት ግለሰቦች ዩናይትድ ስቴትስ ኢራን ላይ ለጥቃት በተጠቀመችበት አንድ የእንግሊዝ አየር ኃይል ጦር ሠፈር አካባቢ በሽብር ተግባር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ
#sbsaudiopodcastMon, 28 Sep 2026 - 06min - 6150 - " እንኳን ለደመራ እና የመስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ " - መላከ አርያም ቀሲስ ተስፋ ህሩይ
መላከ አርያም ቀሲስ ተስፋ ህሩይ በሜልበርን የደብረሰላም መድሃኒአለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ፤ የዘንድሮውን በአል አስመልክተው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
#sbsaudiopodcastSun, 27 Sep 2026 - 04min - 6149 - ኒውዮርክ ላይ የተከፈተው የተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ የሞቁና የከረሩ አተያዮች ገጠሙትWed, 23 Sep 2026 - 07min
- 6148 - የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ቢሮ የሥራ አጥነት ምጣኔ 9.6 በመቶ ደርሷል አለWed, 23 Sep 2026 - 10min
- 6147 - "አቀላለጠው" በድምፃዊት ዓለም ከበደMon, 20 Feb 2017 - 12min
- 6146 - " 'አተረማመሰው' ሸፈን ብሎ ስሜት እንዲሰጥ ተደርጎ ነው የተዘፈነው፤ ሙሉ በሙሉ ስለ ወሲብ አይደለም" ድምፃዊት ዓለም ከበደTue, 22 Sep 2026 - 18min
- 6145 - "እንኳን ለአዲሱ ዓመትና ብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ፤ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን፤ ዕድራችንን ተቀላቀሉ" በፐርዝ የኢትዮ - አውስትራሊያ መረዳጃ ዕድር
በፐርዝ የኢትዮ - አውስትራሊያ መረዳጃ ዕድር ሊቀመንበር አቶ መስቀሉ ደሴና ኢንጂነር ተስፋዬ ይመር በፐርዝ የኢትዮ - አውስትራሊያ መረዳጃ ዕድር ዐቃቤ ንዋይ፤ ስለ መረዳጃ ዕድሩ የምስረታ ሂደት፣ ቅዳሜ መስከረም 16 / ሴፕቴምበር 26 በጥምረት ሊያከብሯቸው ስላሰቡት የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት 2019 እና የመስቀል በዓል መሰናዶ ይናገራሉ።
#sbsaudiopodcastMon, 21 Sep 2026 - 21min - 6144 - የክልል መንግሥታት ከሠራተኞች ደመወዝ ላይ እስከ ሁለት በመቶ የሚደርስ ክፍያ ሊቀርጡ ነውMon, 21 Sep 2026 - 10min
- 6143 - አውስትራሊያ ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ምክር ቤት አባልነት ይፋ የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ ጀመረች
አውስትራሊያውያን ረጅም ዕድሜና ጤናማ ሕይወትን እንደሚኖሩ - ግና የልጆቻቸው ቁጥር አነስተኛ እንደሚሆን መንግሥታዊው ትውልድ ተሻጋሪ ሪፖርት አመለከተ
#sbsaudiopodcastMon, 21 Sep 2026 - 08min - 6142 - "ልጆችን ቋንቋቸውንና ባሕላቸውን ማስተማር ሀብት ማውረስ ነው፤ ማንነታቸውንም ማሳወቅ ነው" ዶ/ር በላቸው ጨከነ
ዶ/ር በላቸው ጨከነ የAmharicLab የጋራ መሥራች፤ በቅርቡ በይፋ የአማርኛ ቋንቋ ንባብና ፅሑፍ ስለ ጀመረው የዲጂታል መማሪያ ድረ-ገፅ አጠቃቀምና አስተምህሮት ያስረዳሉ።
#sbsaudiopodcastThu, 17 Sep 2026 - 21min - 6141 - የዓለም ባንክ 'ከ90 በመቶ በላይ የኢትዮጵያ የሕክምና ተማሪዎች በሚያገኙት ስልጠና ደስተኛ አይደሉም' አለWed, 16 Sep 2026 - 07min
- 6140 - የንግድ ተቋማት የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት የእራሱን የኢሚግሬሽን ፖሊሲ ይፋ እንዲያደርግና የዋን ኔሽን ፖሊሲ ለምጣኔ ሃብት ድቅቀት እንደሚዳርግ አሳሰቡ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋዛ ውስጥ ከፍርስራሾች ስር ተቀብረው የተገኙ አስከሬኖች ምናልባትም በዓለም አቀፍ ሕግ ጥሰት ሊያስፈርጁ እንደሚችል አመላከተ
#sbsaudiopodcastWed, 16 Sep 2026 - 05min - 6139 - "አውስትራሊያውያን የጎዳና ተዳዳሪዎችን እየረዳን ነው፤ አግዙን፣ተባበሩን። መልካም አዲስ ዓመት!" ወ/ሮ አዳነች ገብረማሪያምና ወ/ሮ ዘነበች በፈቃዱ
ወ/ሮ አዳነች ገብረማርያም የKulture Bridge መሥራችና ሊቀመንበር እና ወ/ሮ ዘነበች በቀለ የ Kulture Bridge መሥራችና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፤ ድርጅታቸው ለአውስትራሊያውያን የጎዳና ተዳዳሪዎች እያበረከተ ስላለው የበጎ አድራጎት ሥራዎች ይናገራሉ። መስከረም 16 / ሴፕቴምበር 26 ቅዳሜ በ153 Rainbow St, Sandgate ባሰናዱት የኢትዮጵያ 2019 አዲስ ዓመት ልዩ ዝግጅት ላይም የብሪስበንና አካባቢዋ ነዋሪ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች አፍሪካውያውያን - አውስትራሊያውያንም በሥፍራው እንዲታደሙ ይጋብዛሉ።
#sbsaudiopodcastWed, 16 Sep 2026 - 09min - 6138 - "አዲሱን ዓመት በፍቅርና በአንድነት እንድናከብር እንጋብዛችኋለን" ወ/ት ገነት ማስረሻ
ወ/ት ገነት ማስረሻ በቪቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ምክትል ፕሬዚደንት፤ ቅዳሜ መስከረም 9 / September 19 በ Kensington Town Hall, 30-34 Bellair St, Kensington በማኅበሩ አስተናጋጅነት ስለሚከበረው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት 2019 ልዩ የበዓል ዝግጅት ፕሮግራም ያስረዳሉ።
#sbsaudiopodcastTue, 15 Sep 2026 - 04min - 6137 - የአንድ አውስትራሊያዊ አባትና ሁለት ሕፃናት ልጆች ሕይወት ባሊ - ኢንዶኔዥያ ውስጥ አለፈMon, 14 Sep 2026 - 06min
- 6136 - "አዲሱ ዓመት የጤና፣ የመተሰሳብና የፍቅር እንዲሆንልን፤ ሰላምንም ይዞ እንዲመጣልን ጥልቅ ምኞታችንን እንገልጣለን" በፐርዝ የኢትዮ- አውስትራሊያ መረዳጃ ዕድር
አቶ ብሩክ የማ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያን የመረዳጃ ዕድር ፀሐፊ፤ ስለ ዕድሩ አመሠራረትና ተልዕኮ ያስተዋውቃሉ። የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውንም በዕድሩ ስም ያስተላልፋሉ።
#sbsaudiopodcastMon, 14 Sep 2026 - 03min - 6135 - "አዲሱ አመት የታሰሩት የሚፈቱበት የተፈናቀሉት ወደቤታቸው የሚመለሱበት የወደቁት የሚነሱበት ፍቅር እና አንድነት የሚሰፍንበት የበረከት አመት ይሁንልን ።" መላክ ጸሃይ ቀሰስ መንግስቱ ሀይሌ
እንኳን 2019 የኢትዮጵያውያን አዲስ አመት አደረሰን መላክ ጸሃይ መንግስቱ ሀይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ የምስራቅ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ አህጉረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ እንዲሁም የብሪዝበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ
#sbsaudiopodcastFri, 11 Sep 2026 - 06min - 6134 - የዘንድሮው አዲስ አመት አይኖቻችንን ዘለአለማዊ ተስፋ ወደሚሆነው እግዚአብሄር የምናነሳበት ፤ ተስፋ የቆረጡ በአዲስ ተስፋ የሚታደሱበት ፤ እርሱን የሚፈልጉት ሁሉ የሚያሻቸውን የሚያገኙበት ይሁንልን ። ” ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ
የዘንድሮው አዲስ አመት አይኖቻችንን ዘለአለማዊ ተስፋ ወደሚሆነው እግዚአብሄር የምናነሳበት ፤ ተስፋ የቆረጡ በአዲስ ተስፋ የሚታደሱበት ፤ እርሱን የሚፈልጉት ሁሉ የሚያሻቸውን የሚያገኙበት ይሁንልን ። ” ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ በዘጸአት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፓስተር
#sbsaudiopodcastFri, 11 Sep 2026 - 05min - 6133 - " አዲሱ አመት አዲስ ነገርን ፤ ፍቅርን ፤ መቻቻልን ፤ ጤናን እና ሰዎች የተመኙትን የሚያገኙበት ይሁንልን "- ሼክ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር
አዲሱ አመት አዲስ ነገርን ፤ ፍቅርን ፤ መቻቻልን ፤ ጤናን እና ሰዎች የተመኙትን የሚያገኙበት ይሁንልን ሲሉ ሼክ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር በአውስትራሊያ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሪ መለክታቸውን አስተላልፈዋል ::
#sbsaudiopodcastThu, 10 Sep 2026 - 02min - 6132 - "መልካም የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት - ዕንቁጣጣሽ!" የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ እና የተቀዋሚ ቡድን መሪ አንገስ ቴይለር
የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ እና የተቃዋሚ ቡድን መሪ አንገስ ቴይለር ለኢትዮጵያውያን አውስትራሊያውያንና ኢትዮጵያውያን የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ያቀርባሉ።
#sbsaudiopodcastThu, 10 Sep 2026 - 05min - 6131 - አዲስ ኮከብ - ድምፃዊ ጴጥሮስ ማስረሻ
በአዲስ አንፀባራቂ ኮከብነት ስሙ እየተነሳ ያለው ድምፃዊ ጴጥሮስ ማስረሻ፤ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ከጋይንት ንፋስ መውጫ እስከ ፋና ላምሮት አይዶል አሸናፊነት እንደምን እንደበቃ ያወጋል። በ2019 አዳዲስ ዘፈኖቹን በአልበም አካትቶ ለኢትዮጵያውያን እነሆኝ ለማለት መሰናዳቱንም ያበሥራል።
#sbsaudiopodcastThu, 10 Sep 2026 - 27min - 6130 - "2019 ተስፋን ይዞ፣ የደከምንበት የሚያፈራበት፣ ሐዘናችን በደስታ የሚቀየርበት፣ መከፋታችን በፈገግታ የሚተካበት ዓመት እንዲሆንልን ምኞቴ ነው" ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ
ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ - የኩዊንስላንድ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፀሐፊ፤ የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት።
#sbsaudiopodcastWed, 09 Sep 2026 - 04min - 6129 - የሃይማኖት አባቶች የ2019 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት መልዕክት በሜልበርን - ፉትስክሬይ ፓርክ
የ2019 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ቅበላ የሃይማኖት መሪዎች መልዕክትና መንፈሳዊ ዝማሬዎች ቅዳሜ ነሐሴ 30 በሜልበርን - ፉትስክሬይ ፓርክ።
#sbsaudiopodcastWed, 09 Sep 2026 - 09min - 6128 - የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት የማኅበራዊ ሚዲያ ዲጂታል ደህንነት ጥበቃ ረቂቅ ሕግ በሳንሱር ተፈርጆ ትችት ተሰነዘረበትWed, 09 Sep 2026 - 06min
- 6127 - የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) 'ሠራተኞች ማኅበራትን ማደራጀታቸውና መብታቸውን መጠየቃቸውን እንደ ተቃውሞና ችግር ፈጣሪነት መታየት የለበትም' ሲል አሳሰበMon, 07 Sep 2026 - 11min
- 6126 - "የመልካም አዲስ ዓመት ምኞቴን በኤምባሲው ዲፕሎማቶችና በራሴ ስም አቀርባለሁ" አቶ ያለለት ጌታቸው - በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ተወካይ ጉዳይ ፈፃሚ
አቶ ያለለት ጌታቸው - በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ተወካይ ጉዳይ ፈፃሚ፤ በአውስትራሊያ ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ አውስትራሊያውያን የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞትና የመጪ ሥራ ዘመን አገልግሎቶችን ያስመለከተ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።
Mon, 07 Sep 2026 - 04min - 6125 - "የዘመን መቁጠሪያችን የሚያኮራ ልዩ ሀብታችን፤ የኢትዮጵያዊነት ልዩ ሥርዓታችንም ነው" ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ
ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያ ዘውድ ምክር ቤት ፕሬዚደንት፤ በሀገር ውስጥና በባሕር ማዶ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ የ2019 አዲስ ዓመት መልካም ምኞት መልዕክት።
Mon, 07 Sep 2026 - 03min - 6124 - "መጪው ዓመት የሀገራችን አንድነት የሚፀናበት፤ የሰዎች ማንነት የኩራታቸው ምንጭ ብቻ የሚሆንበት ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ።" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው - በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ አዲሱን 2019 የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ ሕዝባዊ በዓል ምክንያት በማድረግ መልካም ምኞታቸውን ይገልጣሉ።
Mon, 07 Sep 2026 - 02min - 6123 - "አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያ ሀገራችን ሰላምና መረጋጋትን፤ ለወገኖቻችንም ከስጋት ነፃ የሆነ ዓመት እንዲሆን በፅኑ እመኛለሁ" ዶ/ር ለገሰ ጋረደው
ዶ/ር ለገሰ ጋረደው - የደቡብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ አዲሱን 2019 የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ ሕዝባዊ በዓል ምክንያት በማድረግ መልካም ምኞታቸውን ይገልጣሉ።
Mon, 07 Sep 2026 - 04min - 6122 - የ2019 አዲስ ዓመት ቅበላ በሜልበርን ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት አንደበት
የ2019 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ቅበላ ቅዳሜ ነሐሴ 30 በሜልበርን-ፉትስክሬይ ፓርክ በድምቀት ተከብሯል። ኢትዮጵያውያን-አውስትራሊያውያን የበዓሉን መሰናዶ፣ የአዲስ ዓመት ምኞትና ተስፋዎቻቸውን አሰናስለው አጋርተዋል።
Mon, 07 Sep 2026 - 16min - 6121 - የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በ "አዲስ አበባ" አዘጋጅነት በዕለተ ዕንቁጣጣሽ ሜልበርን ከተማ ላይ ደምቆ ሊከበር ነው
ወ/ሮ ነፃነት ኃይሌ እና አቶ ቶም ኑናን፤ የ New Flower Sound 2019 የኢዮሃ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ልዩ ዝግጅት አስተባባሪዎች፤ ዓርብ መስከረም 1 ቀን / September 11 በ 342 High St, Northcote ከ 6:00 pm እስከ 11:00 pm ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ታዳሚዎች ስላዘጋጁት ልዩ ኩነት ያስረዳሉ። የኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና አውስትራሊያውያን ማኅበረሰብ አባላት የአዲስ ዓመት ታዳሚ እንዲሆኑ ያጋብዛሉ።
Fri, 04 Sep 2026 - 09min - 6120 - "2019 የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ምኞቱ ዕቅዶቹ የሚሳኩበት የሰላም ዓመት ይሁንልን!" ደራሲ ታክሎ ተሾመ
የሜልበርን - አውስትራሊያ ነዋሪ፣ ደራሲ ታክሎ ተሾመ፤ መጪውን የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት አስመልክተው ለመላ ኢትዮጵያውያን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።
Thu, 03 Sep 2026 - 01min - 6119 - #118 Losing a job (Med) - #118 Losing a job (Med)
Learn English for talking about losing your job. Practise ways to explain workplace changes and sympathetic responses to someone who has had bad news. - ከሥራ መሰናበትን አስመልክተው ለመናገር እንግሊዝኛን ይማሩ። የሥራ ቦታ ለውጦችን እንዴት ማብራራት እንደሚቻል እና መጥፎ ዜና ለገጠመው ሰው ርኅራኄ የተመላበት ምላሽ አሰጣጥን ይለማመዱ።
Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here.
- ከእዚህ ክፍለ ዝግጅት ቃለ ሐረጎችን ይለማመዱ፤ የቀሰሙትንም ዕውቀት በዕንቆቅልሻችን እዚህ ይፈትኑ።Thu, 03 Sep 2026 - 10min - 6118 - በሳዑዲ አረቢያ በፍልሰተኞች መካከል በቅርቡ ከተከሰተ የቡድን ግጭትና ግድያ ጋር በተያያዘ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን ተያዙWed, 02 Sep 2026 - 08min
- 6117 - የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት በደርዘኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ኔፓል ውስጥ የደረሱበት አለመታወቅ በእጅጉ እንዳሳሰበው አስታወቀWed, 02 Sep 2026 - 05min
- 6116 - ኔፓል ውስጥ የደረሱበት አልታወቀም የተባሉ አውስትራሊያውያን ቁጥር ጨመረMon, 31 Aug 2026 - 04min
- 6115 - የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ላይ የቀረቡ ምክረ ሃሳቦችን አተገባበር የሚከታተል ገለልተኛና ሕጋዊ አካል እንዲቋቋም ጠየቀMon, 31 Aug 2026 - 10min
- 6114 - "ኢትዮጵያዊነታችንን ካላስቀደምንና በጎሳ አካሔድ የሚኬድ ከሆነ፤ አሁን እንኳ የተረፈችዋን ኢትዮጵያ ላናገኛት እንችላለን" የቀድሞው ጠ/ሚ/ር ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ
በሕይወት ዘመናቸው ስለ "እኛና አብዮቱ" መፅሓፋቸው ሲናገሩ "ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መሆኗ ይቆጨኛል፣ ያናድደኛል፣ ያሳዝነኛል። ወደብ አልባ ሀገር ነፃ ሀገር አይደለም። መጪዎቹ የኢትዮጵያ መንግሥታት የሚያስቡበት ጉዳይ ይመስለኛል" ያሉት የቀድሞው የኢትዮጵያ ሕዝባዊት ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ (ኢሕዲሪ) ጠቅላይ ሚኒስትር ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ ዘርፈ ብዙ አተያዮች። (ምልሰታዊ ምልከታ
Fri, 28 Aug 2026 - 28min - 6113 - "የአዲስ አበባን ሀብትና የፖለቲካ ስልጣን መቆጣጠር ኢትዮጵያን መቆጣጠር ተደርጎ በተቀናቃኝ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ቡድኖች ዘንድ በግልፅ ይታያል" ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን
ዶ/ር ዳንኤል ካሳሁን፤ በኦስቲን ኮሙዩኒቲ ኮሌጅ ጂ አይ ኤስ ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ ሰሞኑን "ከፑንት እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ፤ በካሳሁን ሰቦቃ በSBS የተደረጉ ቃለ መጠይቆችና መጣጥፎች" በሚል ርዕስ በዶ/ር ግርማ አውግቸው አርታኢነትና በሴማዊ ጥናቶች መካነ ተቋም አሳታሚነት ለሕትመት በበቃው መፅሐፍ ላይ "የኢትዮጵያ ታሪካዊ የመዲናዎች ዝውውር ጂኦግራፊያዊ ጠባያት" በሚል ርዕሰ መጠሪያ ስላቀረቡት የመጣጥፋቸው ጭብጦች ይናገራሉ።
Wed, 26 Aug 2026 - 14min - 6112 - 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀመረWed, 26 Aug 2026 - 09min
- 6111 - "እኔ ሀገር ያለኝ ሰው ነኝ፤ እንዴት ቢንቁኝ ነው አሜሪካን ሀገር ቀርተህ የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ሁን የሚሉኝ?" የዘመነ ቀ.ኃ.ሥ ኢትዮጵያዊ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ
ፕ/ር ዐቢይ ጣሴ፤ የማኅበራዊ ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ፣ የሞሪታኒያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንትና የትምህርት ሚኒስትር አማካሪ (በወቅቱ)፤ ስለ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችና ፍልሰተኞች ሳቢና ገፊ አስባቦችን አስመልክተው በሜልበርን ዩኒቨርሲቲ ካቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ አንኳር ሃሳቦች ነቅሰው ያስረዳሉ። (ምልሰታዊ ምልከታ)
Tue, 25 Aug 2026 - 13min - 6110 - ለአንድ ወር ከስምንት ቀናት የተካሔደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ አዲስ አበባ የክርክር ምንጭ ሆናው ተጠናቅቋልMon, 24 Aug 2026 - 12min
- 6109 - በኩዊንስላንድ ብቻ ተጨማሪ 46 ሺህ የጤና ባለሙያዎችና 38 ሺህ የኮንስትራክሽን ሠራተኞች እንደሚያስፈልጉ ተመለከተMon, 24 Aug 2026 - 06min
- 6108 - #117 Borrowing books at the library (Med) - #117 Borrowing books at the library (Med)
Learn English useful for visiting a library. Practise everyday phrases for returning borrowed items, asking about late fees and due dates, renewing items, reserving titles, and using the library catalogue. - እንግሊዝኛን ይማሩ ቤተ መጽሐፍን ለመጎብኘት ይጠቅማል። የተዋሱትን ስለ መመለስ፣ ያለተከፈለ የዘገየ ክፍያንና የክፍያ ቀናትን ስለ መጠየቅ፣ የውሰት ቀናትን ማራዘም፣ በስምዎ ተመዝግቦ እንዲቆይ ማድረግንና የቤተ መፅሐፍ የይዘት ማውጫ አዘቦታዊ ቃለ ሐረጎችን ይለማመዱ።
Keep practising the phrases from this episode and test what you’ve learned with our quiz here. - የዚህን ክፍለ ዝግጅታችንን ቃለ ሐረጎች ይለማመዱ፤ የተማሩትንም በዕንቆቅልሻችን እራስዎን እዚህ ይፈትኑ።Thu, 20 Aug 2026 - 14min - 6107 - በወሲባዊ ጥቃት ጥርጣሬ ሳቢያ በአምስት የሲድኒ ስዋንስ እግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ ግደባ ተጣለWed, 19 Aug 2026 - 06min
- 6106 - አዲሱ የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት በ15 ሀገሮች በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ለኢትዮጵያውያን ዜጎች መሰጠት መጀመሩን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገለጠWed, 19 Aug 2026 - 09min
- 6105 - "ለበዓለ ደብረ ታቦር እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን!" መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ጎበና
መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ጎበና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሰሜን አፍሪካ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ ስለ በዓለ ደብረ ታቦር በሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አከባበር ይገልጣሉ። መንፈሳዊ ጥሪም ያቀርባሉ።
Wed, 19 Aug 2026 - 10min - 6104 - ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ኦማን ለዩናይትድ ስቴትስና ኢራን የሰላም ስምምነት ደንቃራ ከሆነች በአሜሪካ ቦምብ ልትጋይ እንደምትችል አስጠነቀቁTue, 18 Aug 2026 - 04min
- 6103 - ‘በርካታ ሠራተኞች የጡረታ አበል ተቀማጫቸውን አስቀድመው ለቤት ብድርና ኑሮ መደጎሚያ ቢያውሉት የተሻለ ሁኔታ ላይ ይሆናሉ’ የሚለው የዋን ኔሽን ዕሳቤ ተቃውሞና ድጋፍ ገጥሞታልMon, 17 Aug 2026 - 08min
Podcasts similar to SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
El Partidazo de COPE COPE
Herrera en COPE COPE
La Linterna COPE
Es la Mañana de Federico esRadio
La noche de Cuesta esRadio
La Trinchera de Llamas esRadio
Hondelatte Raconte Europe 1
Affaires sensibles France Inter
LEGEND Guillaume Pley
CHRONIQUES CRIMINELLES Jacques Pradel - TF1
El colegio invisible OndaCero
La Rosa de los Vientos OndaCero
Les grands dossiers de l'Histoire par Franck Ferrand Radio Classique
Espacio en blanco Radio Nacional
Entrez dans l'Histoire RTL
Le grand récit RTL
Les Grosses Têtes RTL
L'Heure Du Crime RTL
El Larguero SER Podcast
Nadie Sabe Nada SER Podcast
SER Historia SER Podcast
Todo Concostrina SER Podcast
Un Libro Una Hora SER Podcast
HISTORIAS DE LA HISTORIA VIVA RADIO
Other Society & Culture Podcasts
Conversations ABC Australia
Casefile True Crime Casefile Presents
Forensic Files HLN
The Poisoned Wife The Australian
Forbidden History Like A Shot Entertainment
The Diary Of A CEO with Steven Bartlett DOAC
Ukraine: The Latest The Telegraph
Late Night Live — Full program podcast ABC Australia
Barangay Love Stories Barangay LS 97.1 Manila | GMA Network Inc.
C dans l'air France Télévisions
SBS Vietnamese - SBS Việt ngữ SBS
Life Uncut LiSTNR
Unexplained iHeartPodcasts
True Crime Media Network
Legends of the Old West Black Barrel Media
Dear MOR MOR Entertainment
Piers Morgan Uncensored Piers Morgan Uncensored
Australia All Over ABC Australia
Mamamia Out Loud Mamamia Podcasts
Unravel ABC Australia
