Filtrar por género
- 4236 - "ሎሬየት ፀጋዬ ገ/መድኅን የሀገር ዋርካ የሆነ አይተኬ ድንቅ የፈጠራ ሰው ነው፤ እንደ ፀጋዬ ያለ ሰው በምዕተ ዓመት ውስጥ የሚፈጠረው አንዴ ነው" አበራ ለማ
ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማ፤ በድምፃዊ ጌታቸው ካሣ ተዘፍኖ ዘመን ተሻጋሪ ስለ ሆነው "ሀገሬን አትንኳት" ግጥሙ፣ ስለ ባለ ቅኔ ሎሬየት ፀጋዬ ገብረመድኅን ዘርፈ ብዙ ተጠባቢነትና ወዳጅነት አንስቶ ይናገራል። ሥነ ግጥሞቹንም ያስደምጣል።
Sat, 04 May 2024 - 17min - 4235 - "ሥነ ፅሑፍ ቁራኛ ነው፤ ከፀሐፊው ጋር በፍቅርም በትንቅንቅም ተያይዘው ይዘልቃሉ፤ አይላቀቁም" ጋዜጠኛና ደራሲ አበራ ለማSat, 04 May 2024 - 18min
- 4234 - "ጋዜጠኛ በንፁህ ኅሊናው ሚዛናዊ የጋዜጠኛነት ሥራን መሥራት እንጂ፤ ሙያውን የሚያራክስ ነገር መሥራት የለበትም። አሁን እንደወረርሽኝ የወረረን እሱ ነው" አበራ ለማSat, 04 May 2024 - 14min
- 4233 - አበራ ለማ፤ ከመምህርነት ወደ ጋዜጠኛነትና ደራሲነት
ከኢትዮጵያ አንጋፋና ስመ ገነን ጋዜጠኞችና ደራሲዎች ውስጥ ቀዳሚ ተጠቃሽ ከሆኑቱ ውስጥ አበራ ለማ አንዱ ነው። በማስታወቂያ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ራዲዮና አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ በግሉ ፕሬስ በአዕምሮ ጋዜጣ የጋዜጠኛነት ድርሻውን አበርክቷል። በድርሰት በረከቶቹም ሰሞነኛውን "የዓለማችን ምስጢራት" መፅሐፉን አክሎ ከ20 በላይ መፅሐፍትን ለተደራሲያን እነሆኝ ብሏል።
Fri, 03 May 2024 - 12min - 4232 - Understanding the profound connections First Nations have with the land - ነባር ዜጎች ከመሬታቸው ጋር ያላቸውን ጥልቅ ቁርኝቶች መረዳት
The land holds a profound spiritual significance for Aboriginal and Torres Strait Islander peoples, intricately intertwined with their identity, belonging, and way of life. - ለአቦርጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች መሬት ጥልቅ መንፈሳዊ ፋይዳን የያዘ፣ ከማንነታቸው፣ ውሁድነትና የአኗኗር ዘዬ ጋር ተጋምዶ የተቆራኘ ነው።
Thu, 02 May 2024 - 07min - 4231 - ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ለሚከናወነው የሽግግር ፍትሕ ሂደት ድጋፍ እያደረገች መሆኗን አስታወቀችWed, 01 May 2024 - 09min
- 4230 - “ ግላኮማን አንዴ ከተከሰተ ባለበት ማቆም እንጂ ሙሉ ለሙሉ ማዳን አይቻልም ” - ዶ /ር ለምለም ታምራት
ዶ /ር ለምለም ታምራት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ የዓይን ሐኪምና የግላኮማ ስፔሽያሊስት (ልዩ ሐኪም ) የዓይን ውስጥ ዕብጠት ግላኮማ ምንም አይነት ምልክቶችን ሳያሳይ ዕይታችንን ሊጋርድ የሚችል በሽታ መሆኑን ያስረዳሉ።
Wed, 01 May 2024 - 16min - 4229 - ሰሙነ ህማማት እና ትርጓሜው - በመጋቢ ሐዲስ ብሩክ ተስፋዬ
መጋቢ ሐዲስ ብሩክ ተስፋዬ በሜልበርን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ስብከተ ወንጌል ሀላፊ ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አማንያን ዘንድ በተለየ ሁኔታ የሚታሰቡትን የሰሙነ ህማማት ቀናት ትርጓሜ አስረድተዋል ።
Wed, 01 May 2024 - 16min - 4228 - "ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም በዓለ ትንሣኤን እንመኛለን" በሜልበርን-አውስትራሊያ የሰንበት ት/ቤት ዘማሪያን
በአገረ አውስትራሊያ-ሜልበርን ከተማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤልና የመካነ ሰላም ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት መዘመራን፤ ቤተልሔም ትዕግስቱ፣ ፅዮን ብሩክ፣ ኤማንዳ ወንድወሰንና ኤፍራታ ሚሊዮን ሰሙነ ሕማማትን ምክን ያት በማድረግ "በጌቴ ሰማኔ" መንፋሳዊ መዝሙርን ያሰማሉ።
Tue, 30 Apr 2024 - 11min - 4227 - ዜና - በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል የአውስትራሊያ ፓርላማ የአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ አደረገMon, 29 Apr 2024 - 06min
- 4226 - በአዲስ አበባ ከ28 ሀገራት የተውጣጡ ከ77 ሺህ በላይ ስደተኞች እንደሚኖሩና 92 በመቶው ኤርትራውያን መሆናቸው ተገለጠMon, 29 Apr 2024 - 08min
- 4225 - የአንዛክ ቀን በመላው አውስትራሊያና በባሕር ማዶ ተከበረ
የአውስትራሊያ ፌዴራል ፖሊስ ከእምነት መሪዎች ጋር መክረናል ሲል፤ በሲድኒ የእስልምና እምነት መሪዎች አሰሳውን አስመልክቶ "እንድናውቀው" እንጂ "እንድንመክርበት" አልተደረገም ይላሉ
Thu, 25 Apr 2024 - 04min - 4224 - #60 Talking about commemorating | Anzac Day (Med)
Learn how to talk about commemorating Anzac Day, plus find out why it's important for all Australians.
Thu, 25 Apr 2024 - 16min - 4223 - በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመግታት የድርጊት እርምጃ ጥሪ ቀረበWed, 24 Apr 2024 - 06min
- 4222 - በኢትዮጵያ 56 በመቶ የሁለተኛና ሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብ እንደማይችሉ ተገለጠ
ከየመን የባሕር ዳርቻ ወደ ጂቡቲ ስትጓዝ በነበረች አንዲት ጀልባ ላይ በደረሰ አደጋ ተሳፋሪ ከነበሩት 77 ኢትዮጵያውያን ውስጥ 5 ሕፃናትንና ሴቶችን ጨምሮ የ16 ዜጎች ሕይወት አለፈ
Wed, 24 Apr 2024 - 06min - 4221 - Tackling misinformation: How to identify and combat false news - ሐሰተኛ መረጃን መገደብ፤ ሐሰተኛ ዜናዎችን እንደምን መለየትና መፋለም እንደሚቻል
In an era where information travels at the speed of light, it has become increasingly difficult to distinguish between true and false. Whether deemed false news, misinformation, or disinformation, the consequences are the same - a distortion of reality that can affect people's opinions, beliefs, and even important decisions. - መረጃ በብርሃን ፍጥነት በሚጓዝበት ዘመን፤ እውነትና ሐሰቱን ለመለየት አዋኪነቱ እየጨመረ መጥቷል። ሐሰተኛ ዜናዎች፣ ሐሰተኛ መረጃም ይሁን ወይም አሳሳች መረጃ ይባሉ መዘዞቻቸው ተመሳሳይ ነው፤ የሰዎችን አተያዮችና አመኔታዎች በማዛባት ሲልም ጠቃሚ ውሳኔዎች ላይ ተፅዕኖን ያሳድራሉ።
Wed, 24 Apr 2024 - 12min - 4220 - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የትጥቅ ታጋዮች በሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረበ፤ ጥበቃም እንደሚደረግላቸው ገለጠTue, 23 Apr 2024 - 03min
- 4219 - በጅሮንድ ቻልመርስ የአውስትራሊያ የወደፊት የምጣኔ ሃብት ዕድገት ትንበያን አለዝበው ገለጡMon, 22 Apr 2024 - 08min
- 4218 - "የጋምቤላ ችግር መታየት ያለበት የኑዌሮችና አኟኮች ተደርጎ ሳይሆን፤ ኢትዮጵያን ከደቡብ ሱዳን ጋር ሊያዋጋ የሚችል አሳሳቢ ጉዳይ ሆኖ ነው" ዶ/ር ኦፒዎ ቻም
ዶ/ር ኦፒው ኦሙት ቻም፤ የቀድሞ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት፤ ጋምቤላ ክልል ውስጥ ተከስተው ስላሉት ዋነኛ ችግሮች፣ መንስዔዎችና ምክረ ሃሳቦችን አንስተው ይናገራሉ።
Mon, 22 Apr 2024 - 15min - 4217 - የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይና አማራ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ውጥረት በአገራዊ ምክክር ሂደቱና በኮሚሽኑ ዕቅዶች ላይ ስጋት እንደሚፈጥር ገለጠMon, 22 Apr 2024 - 06min
- 4216 - "በሐረሪ ሕብረተሰብ ውስጥ 40 ያህል የአለላ ስፌት ዓይነቶች መኖራቸውን ጥናቶች ያመለከታሉ" ወ/ሮ ውዳድ ሳሊምSat, 20 Apr 2024 - 16min
- 4215 - የዓለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያ በረሃብና ተላላፊ በሽታ እየተፈነች እንደሆነና ከፍ ያለ የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያሻት አሳሰበ
የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት 'ሕወሓት ወረራ ፈፅሞብኛል' ሲል ለፀጥታ አካላት፣ ለነዋሪዎች፣ የፌዴራል መንግሥትና ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አስታወቀ፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከፌዴራልና የአማራ ክልል መንግሥታት ጋር ግጭት ውስጥ አይደለሁም አለ
Thu, 18 Apr 2024 - 05min - 4214 - የኤልያስ ዋንጫ፤ "ኤልያስ አገራችን ካፈራቻቸው የእግር ኳስ ተጫዋቾች በጣም ለየት ያለ ተጫዋች ነው" አቤል አስመላሽ
በአዘጋጅና ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ "የኤልያስ ዋንጫ" በሚል ስያሜ የቀድሞውን የመብራት ኃይልና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋች ኤልያስ ጁሐርን ግለ ታሪክ የዘገበ ፊልም እሑድ ሚያዝያ 6 ከቀትር በኋላ በሜልበርን ከተማ ለሕዝብ ዕይታ ቀርቧል። ዝነኛ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና ክለብ ተጫዋቾች በሥፍራው ተገኝተው አድናቆታቸውን ገልጠዋል።
Thu, 18 Apr 2024 - 09min - 4213 - በሲድኒ የቤተክርስቲያን ውስጥ ጥቃትን ተከትሎ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የተቃዋሚ ቡድን መሪ የአንድነት ጥሪ አቀረቡ
ኬንያ - ኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት እየተባባሰ ነው በሚል አስባብ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችውን የኤሌክትሪክ ሽያጭ ስምምነት የመከለስ ዕሳቤ እንዳላት ፍንጭ ሰጠች።
Tue, 16 Apr 2024 - 06min - 4212 - ኢትዮጵያ ውስጥ ለሰፈነው የጎሣ ፖለቲካ ኃላፊነት ወሳጅ ማን ነው? የ1966ቱ ተራማጆች ወይስ የወቅቱ የማንነት ፖለቲካ አራማጆች?
የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ "ኢትዮጵያዊነት ሞቷል፤ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ተዳክሟል ሊባል የሚችል አይመስለኝም። ኢትዮጵያን በውስጣቸው ይዘው የሚኖሩ፤ ታማኝ ሆነው ያሉ አሉ። በጎሣ ፖለቲካ ሁሉም ተጎጂ ነው" ሲሉ፤ አቶ አበራ የማነአብ "ኢትዮጵያዊነት ገለል ተደርጎ የሕዝብ አንድነት እንዲሻክር፤ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ወደ ግጭትም እንዲሸጋገር መንግሥት አስተዋፅዖ አለው" በማለት ስለ ጎሣ ተኮር የማንነት ፖለቲካ አንስተው አተያይቸውን ያጋራሉ።
Tue, 16 Apr 2024 - 20min - 4211 - "የመኢሶን ትልቁ አስተዋፅዖ ለውጡ ሕዝባዊ ይዘት እንዲኖረው በመሬት፣ ሕዝባዊ ድርጅቶችና የብሔሮች መብቶች ዙሪያ የተቻለውን ሁሉ ማድረጉ ነው" አቶ አበራ የማነአብ
"የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴና አቶ አበራ የማነ አብ፤ በኢትዮጵያ አብዮታዊ እንቅስቃሴ ወቅት የመላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) ፖለቲካዊ ሚና ነቅሰው ይናገራሉ።
Tue, 16 Apr 2024 - 18min - 4210 - " 'የመኢሶን ሰማዕታት' መጽሐፍ ፋይዳ አንድ ተጨባጭ የሆነ የታሪክ ሰነድ ማቆየት ነው" ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ
"የመኢሶን ሰማዕታት" መጽሐፍ አዘጋጆች ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴና አቶ አበራ የማነ አብ፤ በ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት ወቅት ሕይወታቸውን ላጡ የድርጅታቸው የመላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) አባላት የመዘከሪያ መጽሐፍን መሰናዶና ትሩፋቶቹን አስመልክተው ያስረዳሉ።
Tue, 16 Apr 2024 - 12min - 4209 - የአውስትራሊያ ሰንደቅ ዓላማ በሲድኒ የገበያ ማዕከል በስለት የተገደሉ ስድስት ሰዎችን በክብርና በሐዘን ለመዘከር በግማሽ ዝቅ ብሏልMon, 15 Apr 2024 - 06min
- 4208 - ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ የምግብ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ከታየባቸው አምስት የአፍሪካ አገራት ውስጥ ተካተተችMon, 15 Apr 2024 - 05min
- 4207 - ዩናይትድ ስቴትስና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የአቶ ባቴ ኡርጌሳን ግድያ አስመልክቶ ገለልተኛና ሙሉዕ ምርመራ እንዲካሔድ ጠየቁThu, 11 Apr 2024 - 04min
- 4206 - #59 Talking about cooking (Med)Thu, 11 Apr 2024 - 13min
- 4205 - ከጂቡቲ ወደ የመን በጀልባ ይጓዙ የነበሩ 38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን አጡWed, 10 Apr 2024 - 07min
- 4204 - "ኢድ አልፈጥር! አገራችንን ኢትዮጵያን ሰላም ያድርግልን፤ ደም ማፍሰሱን አላህ በኃይሉ ያስተካክልልን" ሼክ አብዱራህማን ሐጂ ከቢር
ሼህ አብድራህማን ሐጂ ከቢር በአውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን እስልምና እምነት ተከታዮች መሪ ፤ የዘንድሮውን ኢድ አል ፈጥር በዓልን አስመልክተው የፆምና ፀሎት መንፈሳዊ ፋይዳዎችንና የሰላም ምኞታቸውን አሰናስለው ይገልጣሉ።
Wed, 10 Apr 2024 - 08min - 4203 - አውስትራሊያ ውስጥ ከ2035 አንስቶ በነዳጅና በናፍጣ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ለሽያጭ እንዳይውሉ ጥሪ ቀረበTue, 09 Apr 2024 - 03min
- 4202 - ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄ ድርድር ሊቀጥል ነውTue, 09 Apr 2024 - 09min
- 4201 - በአዲሱ የምግብና ግሮሰሪ ሥነ ምግባር ደንብ ሱፐርማርኬቶች እስከ 10 ሚሊየን ዶላርስ የሚደርስ መቀጮ ሊያገኛቸው ነውMon, 08 Apr 2024 - 06min
- 4200 - "ኤልያስ ካለ ጎል አለ፤ አብዛኛዎቹ የመብራት ኃይል ቡድን ዋንጫዎች የኤልያስ ጁሐር ዋንጫዎች ናቸው" የፊልም ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ
"የኤልያስ ዋንጫ" አዘጋጅና ዳይሬክተር ዐቢይ አየለ፤ የቀድሞውን የመብራት ኃይልና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋች ኤልያስ ጁሐርን ግለ ታሪክ በዘጋቢ ፊልም ቀርፀው ለሕዝብ ዕይታ ለማቅረብ ስለምን እንደወደዱና የፊልሙን ጭብጥ አሰናስለው ይናገራሉ። "የኤልያስ ዋንጫ" በሳምንቱ መጨረሻ በሜልበርን - አውስትራሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ ዕይታ በነፃ ይቀርባል።
Mon, 08 Apr 2024 - 11min - 4199 - " የደብረ ዘይት በዓልን ስናከብር የክርስቶስን ዳግም ምጽአት እያሰብን ነው ። ” መልአከ ጽዮን ቀሲስ እንግዳ ቸሩ
መልአከ ጽዮን ቀሲስ እንግዳ ቸሩ በአውስትራሊያ የልደታ ለማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ፤ በትናንትናው እለት የተከበረውን የደብረ ዘይት በዓል ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት ክርስቲያኖች ከመቼው ጊዜ በበለጠ ለኢትዮጵያ እንዲጸልዩ አደራ ብለዋል ።
Mon, 08 Apr 2024 - 09min - 4198 - #58 How to say 'no' at work (Adv)Sun, 07 Apr 2024 - 15min
- 4197 - በነባር ዜጎች መካከል ያለ ባሕላዊ ዝንቅነትን የመረዳት ጠቀሜታ
የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች ከሆኑት የአቦሪጂናልና ቶረስ መሽመጥ ደሴት ሰዎች ጋር ተሳትፎ በማድረግ ትርጉም ያለው ግንኙነቶችን ለመገንባት ካሹ በመካከላቸው ያሉ ባሕላዊ ዝንቅነቶችን መረዳት ግድ ይላል።
Sun, 07 Apr 2024 - 07min - 4196 - ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልበኒዚ የአውስትራሊያዊቷን እርዳታ ሠራተኛ ሞት ተከትሎ የእሥራኤል መንግሥት ኃላፊነት እንዲወስድ ጠየቁWed, 03 Apr 2024 - 04min
- 4195 - " የ29ኛው ኩዊል የጋዜጠኛነት ልህቀት ሽልማት ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያውያንም ጭምር ነው ። "- የኩዊል ሽልማት አሸናፊ ጋዜጠኛ ካሣሁን ሰቦቃ
“ ይህ ታሪክ እንዲህ በቀላሉ የሚነገር አይደለም ፤ ሲያነቡትም ሆነ ሲጽፉት ስሜትን የሚፈታተን ስለሆነ አጠናቅቆ ለማውጣት ስድስት ወራትን ፈጅቷል ። ” ሩቺካ ታልወር
Wed, 03 Apr 2024 - 16min - 4194 - “ ጋዜጠኝነት ለእኔ ሕዝብን እና አገርን በቀናነት ማገልገል ነው ። ” የኩዊል ሽልማት አሽናፊ ጋዜጠኛ ካሣሁን ሰቦቃ
“ በሽልማቱ ላይ ከተገኙት ሰዎች መካከል የኢትዮጵያም ሆነ አፍሪካ ዝርያ ካላቸው የተገኘሁት እኔ ብቻ ነበርኩ ።ይህ የታሪክ አጋጣሚም የሽልማቱን ዋጋ በተለየ ሁኔታ ላቅ ብሎ እንዲታይ አድርጎታል ። ” ለሜልበርን ፕሬስ ክለብ በመድብለባሕል ጉዳዮችና ሚዲያ ዘርፍ በአውስትራሊያ ፕሮፌሽናል ጋዜጠኝነት ሙያ የላቀ ደረጃ ያለውን 29ኛውን የኩዊል የጋዜጠኛንት ልህቀት ሽልማት አሽናፊ ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ “ SBS ታሪኬን ሲያወጣ ከስደተኝነት ባሻገር ለአውስትራሊያ ማኅበረሰብ የማበረክተው እንዳለ እድርጎ አጉልቶ በማሳየቱ በበርካቶች ዘንድ የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲመጣ አድርጓል ። ” ቤተልሔም ጥበቡ
Wed, 03 Apr 2024 - 20min - 4193 - የረመዳን ጾም እና የሴቶች ድርሻ
ወይዘሮ ነጁም አብደላ የረመዳን ጾም ወቅት በመስጠት በረከትን የምንቀበልበት ቅዱስ ወር ነው ይላሉ። ወ/ሮ ነጁም የሜልበርን ነዋሪ እና የአራት ልጆች እናት ናቸው ፤ ምንም እንኳን ልጆቻቸውን ለብቻቸው ቢያሳድጉም ውጤታም ልጆችን ለማውጣት እና እርሳቸውም ያለሙትን የከፍተኛ ትምህርት ግብ ለማጠናቀቅ ብቸኝነታቸው እንዳላገዳቸው ነግረውናል ።
Tue, 02 Apr 2024 - 16min - 4192 - በአዲስ አበባ የከርሰ ምድር ውኃ እየተሟጠጠ ነው ተባለMon, 01 Apr 2024 - 06min
- 4191 - በኩዊንስላንድ የዝናቡ መጠን እንደቀነሰ ቢነገርም ፤ ውኃው እስኪደርቅ ጊዜ ሊፈጅ እንደሚችል ተገለጸMon, 01 Apr 2024 - 06min
- 4190 - በኦሮሚያ ክልል በርካታ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቀሳውስትና ምዕመናን መገደላቸው ተመለከተThu, 28 Mar 2024 - 03min
- 4189 - #57 Talking about ageing (Med)Thu, 28 Mar 2024 - 16min
- 4188 - Australian Easter: Exploring social and cultural traditions beyond religion - በዓለ ትንሣኤ በአውስትራሊያ፤ ከሃይማኖት ባሻገር የማኅበራዊና ባሕላዊ ልማዶች ዳሰሳ
Easter holds great significance for Christians. Yet, for those of different faiths or non-religious backgrounds, it presents a chance to relish a four-day weekend, partake in family and social gatherings, engage in outdoor activities, and attend events where children take centre stage. Here's your essential guide to celebrating Easter in Australia. - በዓለ ትንሣኤ ለክርስቲያኖች ትልቅ ፋይዳ አለው። ይሁንና ለሌላ እምነት ተከታዮች ወይም ከቶውንም አማኝ ላልሆኑቱም፤ የአራት ቀናት የዕረፍት ሐሴትን ይቸራል። በከፊል ለቤተሰብና ማኅበራዊ ስብስብ፣ ከቤት ውጪ እንቅስቃሴዎች ተሳትፎና ልጆች ማዕከላዊ መድረኩን ለሚይዙባቸው ኩነቶች መታደሚያነት። ፋሲካን አውስትራሊያ ውስጥ ለማክበር አሥፈላጊ መመሪያዎን እነሆን።
Wed, 27 Mar 2024 - 10min - 4187 - በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር 'የኢትዮጵያ ውስብስብ ፖለቲካዊና የደህንነት ቀውሶች በውይይት መላ ሊበጅላቸው ያሻል' አሉTue, 26 Mar 2024 - 04min
- 4186 - ስንብት፤ ዶ/ር አንድዓለም ሙላው 1944-2024
"አውስትራሊያ ውስጥ ደስታ ካልሆነ በስተቀር ምንም የገጠመን እንከን የለም" የሚሉት አቶ በሪሁን ካሠኝ፤ ሰሞኑን ከእዚህ ዓለም ስለተለዩት የቀድሞ የትግል አጋራቸው ዶ/ር አንድዓለም ሙላው፤ የከፋኝ ኢትዮጵያ ጀግኖች ግንባር መሪ የግልና ሰብዓዊ አስተዋፅዖዎች አንስተው ይናገራሉ።
Tue, 26 Mar 2024 - 08min - 4185 - #56 Organising a party (Med)Tue, 26 Mar 2024 - 12min
- 4184 - የአውስትራሊያ መንግሥት የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል ከዋጋ ግሽበት ጋር እኩል እንዲራመድ የፍትሓዊ ሥራ ኮሚሽንን ሊጠይቅ ነውMon, 25 Mar 2024 - 07min
- 4183 - በትግራይ ጦርነት ወቅት ምርኮኞች የነበሩ 212 የመከላከያ ሠራዊት አባላት በምሕረት ተለቀቁMon, 25 Mar 2024 - 07min
- 4182 - "ብዙ ስፖንሰሮች ወይም አጋሮች ድጋፋቸውን የሚያበረከቱት ሆይ ሆይታ ለበዛበት ነው፤ በአስተውሎት ሀገርን ለሚያልቁ ሥራዎች ድጋፍ ቢያደርጉ ጠቀሜታ አለው" ደራሲት ሐሊ ሙዘይንSun, 24 Mar 2024 - 15min
- 4181 - "ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን የልብ ትርታ ናት፤ ኢትዮጵያዊነት ልቤ ውስጥ ታትሞ ያለ መቼም የማይፋቅ ሕትመት ነው" ደራሲት ሐሊ ሙዘይንSun, 24 Mar 2024 - 15min
- 4180 - የኢትዮጵያ አየር መንገድ አምስት ታካይ የአገር ውስጥ መዳረሻ አውሮፕላን ማረፊያዎች ግንባታን ጀመረThu, 21 Mar 2024 - 03min
- 4179 - "የዘረኝነት አንዱ ቁልፍ ነገር ጭካኔን ወደ አርበኝነት የመቀየር ኃይል አለው" ዶ/ር ይርጋ ገላው
ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶች ትምህርት ማዕከል ገዲብ ተመራማሪና መምህር፤ በየዓመቱ ማርች 21 ስለሚከበረው ዓለም አቀፉ የፀረ ዘርኝነትና አውስትራሊያ አቀፉን አካታች የብዝኅነት ስምምነት ቀን (Harmony Day) አስመልክተው ይናገራሉ።
Thu, 21 Mar 2024 - 10min - 4178 - "ዘረኝነት ሰብዓዊነትን ይገድላል፤ ዘረኛ ሰው ሰዎችን የሚያየው በሰውነት ሳይሆን በዘር ነው" ዶ/ር ይርጋ ገላው
ዶ/ር ይርጋ ገላው፤ በከርተን ዩኒቨርሲቲ የሰብዓዊ መብቶች ትምህርት ማዕከል ገዲብ ተመራማሪና መምህር፤ በየዓመቱ ማርች 21 ስለሚከበረው ዓለም አቀፉ የፀረ ዘርኝነትና አውስትራሊያ አቀፉን አካታች የብዝኅነት ስምምነት ቀን (Harmony Day) አስመልክተው ይናገራሉ።
Thu, 21 Mar 2024 - 14min - 4177 - ኢትዮጵያ ውስጥ የእስላማዊ ስልጣኔ መነሻ የት ነው?
ደራሲ ተሾመ ብርሃኑ ከማል - 26 መጻሕፍትን ለንባብ ያበቁ ሲሆን፤ አራት ለሕትመት ያልበቁ መጻሕፍትንም ጽፈዋል። እስከ 2000 የሚደርሱ መጣጥፎችንም አስነብበዋል። ሰሞኑን “እስላማዊ ስልጣኔ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ለአንባቢያን እነሆኝ ባሉት መጣጥፋቸው ላይ ካሰፈሩት ውስጥ በኢትዮጵያ የእስላማዊ ስልጣኔን መነሻና የመንዙማ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ሚናዎችን አስመልክተው ይናገራሉ።ዳግም የቀረበ።
Wed, 20 Mar 2024 - 13min - 4176 - እስላማዊ ስልጣኔ ምንድነው?
ደራሲ ተሾመ ብርሃኑ ከማል - 26 መጻሕፍትን ለንባብ ያበቁ ሲሆን፤ አራት ለሕትመት ያልበቁ መጻሕፍትንም ጽፈዋል። እስከ 2000 የሚደርሱ መጣጥፎችንም አስነብበዋል። ሰሞኑን “እስላማዊ ስልጣኔ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ለአንባቢያን እነሆኝ ባሉት መጣጥፋቸው ላይ ካሰፈሩት ውስጥ የእስላማዊ ስልጣኔ ምንነትንና መገለጫዎቹን አንስተው ይናገራሉ። ዳግም የቀረበ።
Wed, 20 Mar 2024 - 11min - 4175 - ዶናልድ ትራምፕ ተመልሰው ፕሬዚደንት ከሆኑ በዩናይትድ ስቴትስ የአውስትራሊያ አምባሳደር ኬቨን ራድ የቆይታ ጊዜ አጭር እንደሚሆን አመላከቱWed, 20 Mar 2024 - 07min
- 4174 - What are Ramadan and Eid and how are they celebrated in Australia? - ረመዳንና ኢድ ምንድናቸው አውስትራሊያ ውስጥ የሚከበሩትስ እንደምን ነው?
As Muslims in Australia and around the world observe Ramadan, a month-long period of devotion and fasting, in this episode, we explore the religious significance of this holy month. - ሙስሊሞች አውስትራሊያ ውስጥና በመላው ዓለም ረመዳንን በማክበር ራሳቸውን ሰጥተው ለአንድ ወር ፆም በሚፆሙበት ወቅት የቅዱስ ወሩን ሃይማኖታዊ ትሩፋቶች እንቃኛለን።
Tue, 19 Mar 2024 - 07min - 4173 - ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የእርስ በእርስ ግጭቶችን ለማስቆም "ኢትዮጵያ በልጆቿ ትታረቅ" ሲል የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ ጥሪ አቀረበ
የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቱ Human Rights Watch የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት አብዲ ኢሌ ክስ ተቋርጦ መፈታት የወንጀል ተግባርን ያበረታታል ሲል ተቃውሞ አሰማ
Tue, 19 Mar 2024 - 04min - 4172 - #55 Describing personal relationships (Med)Tue, 19 Mar 2024 - 14min
- 4171 - "የአዲስ ፓሪስ መጽሔት ዓላማ ኢትዮጵያውያን የፋሽን ሞዴሎችንና የኢትዮጵያን ቱሪዝም ማስተዋወቅ ነው" አቤል ፊጣMon, 18 Mar 2024 - 16min
- 4170 - ኢሠማኮ ላቀረበው የሠራተኞች የዝቅተኛ ደመወዝ ወለልና የግብር ቅነሳ ምላሽ ካላገኘ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለመነጋገር እንደሚሻ አስታወቀMon, 18 Mar 2024 - 09min
- 4169 - " ጾም ስጋን አድክሞ መንፈስን የሚያበረታ መንፈሳዊ ተግባር ነው ። " - መጋቢ አእላፍ ቀሲስ በቃሉ ዳዊት
መጋቢ አእላፍ ቀሲስ በቃሉ ዳዊት ጾም በሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እመነት ተካታዮች እየጾሙት ያለውን የአብይ ጾም ሀይማኖታዊ ጠቀሜታውን አስመልከተው ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
Sun, 17 Mar 2024 - 13min - 4168 - እሥር ላይ ያሉት የአቶ ክርስቲያን ታደለ ያለ መከሰስ የምክር ቤት አባልነት መብት ተነሳThu, 14 Mar 2024 - 04min
- 4167 - #54 How to talk about predictions (Med)Thu, 14 Mar 2024 - 14min
- 4166 - What is the cultural significance of First Nations weaving? - ስፌት ለነባር ዜጎች ያለው አስፈላጊነት ምን ያህል ነው?
Weaving is one of the most complex and sophisticated examples of First Nations technology and culture. It produces objects of beauty, and the process itself has deep cultural significance. Weaving is a way to share knowledge, connect to people and country, invite mindfulness, and much more. - የእጅ ስፌት ውስብስብና ረቂቅ ከሆኑት የነባር ዜጎች ቴክኖሎጂና ባሕል ውስጥ አንዱ አብነት ነው። የውበት ቁሶችን ይፈጥራል፤ ሂደቱም ጥልቅ ባሕላዊ ፋይዳ አለው። የእጅ ስፌት ዕውቀትን የማጋሪያ መንገድ፣ ሰዎችን ከቀዬአቸው ጋር ማገናኛ፣ አስተውሎትን መጋበዣና ከዚያም ላቅ ያለ ነው።
Tue, 12 Mar 2024 - 10min - 4165 - #53 How to give encouragement (Med)Tue, 12 Mar 2024 - 13min
- 4164 - "አድዋ ለእኔ ማንነቴ ነው፤ ኢትዮጵያውያን ሁሉም ቦታ ላይ በኩራት የምንገኘው በአድዋ ድል የነፃነት ስሜት ነው" ቅድስት ሰለሞን
128ኛው የአድዋ ድል በዓል በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር አስተባባሪነት ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የአፍሪካ አገራት ማኅበረሰብ ተወካዮች በታደሙበት በሜልበርን - አውስትራሊያ የካቲት 30 / ማርች 9 ተከብሮ ውሏል።
Tue, 12 Mar 2024 - 10min - 4163 - “ እንኳን አደረሳችሁ - ዐቢይ ጾም የተባለውም ጾሙን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለጾመው ነው ። “ - ብፁዕ አቡነ ሉቃስ
ብፁዕ አቡነ ሉቃስ - በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ ገዳማት የበላይ ኃላፊ፣ የምሥራቅ አውስትራሊያና ኒውዚላንድ አኅጉረ ስብከት ሊቀጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፤ "አንድነት ይበርታ፤ ዘር ቆጠራ ይቅር፤ እስላም ክርስቲያን በማለት ማንኛውንም ልዩነት በመተው በአንድነት ፅኑ" በሚል መልዕክታቸው ምዕመናን አገራቸውን በፀሎት እንዲያስቡ ያሳስባሉ።
Mon, 11 Mar 2024 - 07min - 4162 - ተመድ ኢትዮጵያ ውስጥ በድርቅና በጦርነት ምክንያት ከ20 ሚሊየን በላይ እርዳታ ጠባቂዎች መኖራቸውን አመለከተ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 X9 ቦይንግ የመንገደኞች አውሮፕላን ግዢ መፈፀሙንና በ2035 ዓመታዊ ገቢውን 25 ቢሊየን እንዲሁም 67 ሚሊየን መንገደኞችን ለማጓጓዝ መወጠኑን አስታወቀ።
Mon, 11 Mar 2024 - 10min - 4161 - “ እንኳን ለረመዳን ጾም አደረሳችሁ ” - ሼህ አብድራህማን ሐጂ ከቢር
ሼህ አብድራህማን ሐጂ ከቢር በአውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን እስልምና እምነት ተከታዮች መሪ ፤ በዘንድሮውን የረመዳን ጾም ምዕመናኑ በተለየ ሁኔታ ለአገራቸው ጸሎት እንዲያደርጉ መንፈሳዊ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።
Mon, 11 Mar 2024 - 04min - 4160 - "በዘርኛነት አዝማሚያ ከቋንቋዬ በስተቀር በሌላ የኢትዮጵያ ቋንቋ አልፅፍም የሚል በጣም ጠባብ የሆነ አመለካከት ያላቸው ሰዎች አሉ" ደራሲና ተርጓሚ ሳህለሥላሴ ብርሃነማርያምSun, 10 Mar 2024 - 14min
- 4159 - "አፄ ቴዎድሮስን የማደንቃቸው ዘመነ መሳፍንትን አሸንፈው የኢትዮጵያን አንድነት ያፀኑ ታላቅ መሪ ስለሆኑ ነው" ደራሲና ተርጓሚ ሳህለሥላሴ ብርሃነማርያም
"አሁን ያለንበት ሁኔታ የሚያስታውሰኝ ከአፄ ቴዎድሮስ በፊት የነበረው ዘመነ መሳፍንት መደገምን ነው፤ ከአብዮቱ በኋላ 200 ዓመታት ወደ ኋላ ነው የመለሱን" የሚሉት አንጋፋው ደራሲና ተርጓሚ ሳህለሥላሴ ብርሃነማርያም፤ ከፍተኛ ተነባቢነት ስላገኘው "የሁለት ከተሞች ወግ" ትርጉም መፅሐፋቸውና ሌሎች በርካታ የድርሰትና ትርጉም ሥራዎቻቸው ያወጋሉ።
Sun, 10 Mar 2024 - 13min - 4158 - ከጉራጊኛ ቃላት ትርጉም ወደ ሥነ ፅሑፍ ዓለም፤ ደራሲና ተርጓሚ ሳህለሥላሴ ብርሃነማርያምSat, 09 Mar 2024 - 16min
- 4157 - "ፍልሰተኛ ሴቶች በባሕር ማዶ ከባሎቻቸው ባሕላዊ አስተሳስብና የአገሬው ዘርኛነት አንስቶ ብዙ ማለፍ ያለባቸው ፈተናዎች ያጋጥማቸዋል" ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም
ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ፤ በብሪስበን ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተርና ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ በሜልበር የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂ፤ በተለይ የባሕር ማዶ ነዋሪ ሴቶችን ስለሚገጥማቸው ባሕላዊና የሴቶች መብቶች ፈተናዎችን አስመልክተው ይናገራሉ።
Fri, 08 Mar 2024 - 11min - 4156 - "በቤት ውስጥ ጥቃት ምክንያት በአውስትራሊያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ውስጥም ከመሞት በላይ፤ ከመኖር በታች በሆነ ሁኔታ የሚኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ" ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ
ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ፤ በብሪስበን ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተርና ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ በሜልበር የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂ፤ የሴቶች መብቶች ጥያቄዎችን በመንቀስ ስለ ዓለም አቀፍ ሴቶች ቀን ፋይዳዎችና ትሩፋቶች ይናገራሉ።
Fri, 08 Mar 2024 - 19min - 4155 - "ኢትዮጵያ ውስጥ ዕድሎችን ከማጣት የተነሳ ለብዙ ሴቶች ሴትነታቸው ዕዳ እንጂ ትርፍ ሆኖ የማታይበት ሁኔታ ነው ያለው" ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ
ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደስ፤ በብሪስበን ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተርና ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ በሜልበር የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂ፤ የሴቶች መብቶች ጥያቄዎችን በመንቀስ ስለ ዓለም አቀፍ ሴቶች ቀን ፋይዳዎችና ትሩፋቶች ይናገራሉ።
Fri, 08 Mar 2024 - 12min - 4154 - #52 How to talk about happy and sad moments (Med)
Learn how to talk about nostalgic moments, when you think about the past and can feel both happy and sad at the same time.
Thu, 07 Mar 2024 - 13min - 4153 - Are you eligible for the Higher Education Loan Program? - ለከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም ብቁ ነዎት?
Around three million Australians have a government loan through HELP, the Higher Education Loan Program. You too may be eligible to defer your tertiary tuition fees until you secure a job. - ሶስት ሚሊየን ያህል አውስትራሊያውያን በከፍተኛ ትምህርት ብድር ፕሮግራም በኩል ከመንግሥት ተበድረዋል። ምናልባትም እርስዎም ሥራ እስከሚያገኙ ድረስ የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ክፍያዎን ለማሸጋገር ብቁ ይሆኑ ይሆናል።
Thu, 07 Mar 2024 - 07min - 4152 - "በእምነት ሳትለያዩ ሰው በመሆናችሁ ብቻ ሰው የሆኑትን ለመታደግ መላ ፍጠሩ፤ ለእግዚአብሔር ምክንያት ሆናችሁ ወገናችሁን ታደጉ" አቡነ ኤርሚያስ
ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ወሎ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ መጋቢት 7 / ማርች 16 በሰሜን ወሎ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ለመታደግ በአውስትራሊያ ስለሚካሔደው የበጎ አድራጎት ችሮታ ዕሳቤና ከ30 ሺህ በላይ ስለሆኑቱ ተፈናቃዮች የዕለት - ተዕለት ሕይወትን የማቆያ ትግል ሁኔታዎች ይናገራሉ።
Wed, 06 Mar 2024 - 10min - 4151 - "የአድዋ ድል አልገዛም ባይነትና የዛሬ ማንነታችንን ጠብቀን የቆየንበት ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛውና ወ/ት ገነት ማስረሻ
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ምክትል ፕሬዚደንትና ወ/ት ገነት ማስረሻ፤ የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር የሕዝብ ግኑኝነት ኃላፊ፤ ቅዳሜ የካቲት 30 / ማርች 9 በማኅበሩ አስተባባሪነት ስለሚዘከረው 128ኛው የአድዋ ድል በዓል ልዩ ዝግጅትና የወደፊት ትልሞች ይናገራሉ።
Wed, 06 Mar 2024 - 22min - 4150 - "ወንድሞቻችን፣ ባሎቻችንና አባቶቻችን ሴቶችን በውጭ ብቻ ሳይሆን በቤት ውስጥ ሥራም በመርዳት እንዲተባበሩን እንጠይቃለን" ወ/ሮ ጽጌ መርጊያ
የኦሮሞ እናቶች/ሴቶች የምስጋና ቀን እሑድ ማርች 3 / የካቲት 24 ሜልበርን ከተማ ውስጥ ተካሂዶ ውሏል። የዝግጅቱ ስተባባሪዎችና ታዳሚዎች አተያያቸውን ያጋራሉ።
Tue, 05 Mar 2024 - 07min - 4149 - #51 Check-in at the airport (Med)Mon, 04 Mar 2024 - 15min
- 4148 - "ውስጣችን ያለውን ችግር ተነጋግረን እንፍታ፤ አድዋ ላይ እንድናሸንፍ ያደረገን አንድነታችን ነው" አሳታሚ ኤልያስ ወንድሙSun, 03 Mar 2024 - 11min
- 4147 - "የነፃነት አርማ ካለን ከባንዲራችን ቀጥሎ ምኒልክ ናቸው" አሳታሚ ኤልያስ ወንድሙSun, 03 Mar 2024 - 18min
- 4146 - “ዋ አድዋ!” - 128ኛ ዝክረ ድልFri, 01 Mar 2024 - 02min
- 4145 - “የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀደም ሲል በኢትዮጵያዊነት ስሜት በአንድነት የተነሳውና ሁልጊዜም የሚነሳው በአድዋ መንፈስ ነው” ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴFri, 01 Mar 2024 - 19min
- 4144 - የኦሮሞ እናቶች/ሴቶች የምስጋና ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ በሜልበርን ሊከበር ነው
የኦሮሞ እናቶች/ሴቶች የምስጋና ቀን አስተባባሪዎች አቶ አብደታ ሁማና አቶ ዓለማየሁ ቁቤ፤ ቅዳሜ ማርች 3 / የካቲት 24 በሜልበርን ከተማ ስለሚካሔደው ልዩ ዝግጅት ያስረዳሉ።
Thu, 29 Feb 2024 - 06min - 4143 - #50 Let's go fishing! (Med)Thu, 29 Feb 2024 - 15min
- 4142 - "የአድዋን ድል በዓል የማከብረው በአንድ ወቅት አንድ እና ታላቅ እንደነበርን ስለሚያስታውሰኝ ነው" አንዲት የአዲስ አበባ ነዋሪWed, 28 Feb 2024 - 10min
- 4141 - "የስደተኞች ወደ ናሩ ዕገታ ማዕከል መወሰድ ልቤን በጣም ነው የሰበረው፤ የእኛም አውስትራሊያ የመቆየት ጉዳይ የተወሰነ ስላልሆነ ሁላችሁም ፀልዩልን" ቤተልሔም ጥበቡ
በናሩና ብሪስበን ዕገታ ማዕከላት ለአራት ዓመትታ የቆየችውና አሁንም በየስድስት ወራት ታዳሽ በሆነ ጊዜያዊ የመቆያ ቪዛ አውስትራሊያ ውስጥ የምትገኘው ቤተልሔም ጥበቡ የስደተኞች መብቶችም ተሟጋች ናት። ሰሞኑን አገር አቀፍ ክርክር በቀሰቀሰው በጀልባ ወደ አውስትራሊያ የዘለቁ ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ናሩ የመላክ ውሳኔን አስመልክታ ትናገራለች። የናሩ ቆይታዋ ያሳደረባትንም ተፅዕኖዎች ታነሳለች።
Wed, 28 Feb 2024 - 12min - 4140 - "የእግር ጉዞው ዓላማ ለትውውቅ፣ ለፍቅር፣ ለአንድነትና ቤተክርስቲያናችንን አጉልቶ ለማሳየት ነው" ዶ/ር ተፈሪ በላይነህ
መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረሥላሴ ጎበና፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪና የሰሜን አፍሪካ ሃገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና ዶ/ር ተፈሪ በላይነህ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይና የእግር ጉዞ አስተባባሪና የግር ጉዞው ተሳታፊዎች ቅዳሜ የካቲት 16 / ፌብሪዋሪ 24 በ "ታላቁ ጉዞ" ስያሜ ስለተካሔደው የእግር ጉዞ ሂደት ይናገራሉ።
Tue, 27 Feb 2024 - 09min - 4139 - የሰላም ስፖርትና ማኅበራዊ ክለብ 10ኛ ዓመቱን በሜልበርን ከተማ አከበረTue, 27 Feb 2024 - 07min
- 4138 - “የኦሮሚያ ክልልን ጨምሮ በብዙ ቦታዎች ለቀጠለው ግጭትና መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ሰላማዊ ውይይትን ከመቀበልና ከመተግበር ውጪ መፍትሔ የለም"ዶ/ር ዳንኤል በቀለMon, 26 Feb 2024 - 10min
- 4137 - ኬንያ 11 በመቶ ዜጎቿ የሚጠቀሙት ዕለታዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ ምንጭ ኢትዮጵያ መሆኗን ገለጠችMon, 26 Feb 2024 - 10min
Podcasts similares a SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
- Conversations ABC listen
- El Partidazo de COPE COPE
- Herrera en COPE COPE
- Es la Mañana de Federico esRadio
- La Noche de Dieter esRadio
- Hondelatte Raconte - Christophe Hondelatte Europe 1
- 財經一路發 News98
- La rosa de los vientos OndaCero
- Más de uno OndaCero
- La Zanzara Radio 24
- L'Heure Du Crime RTL
- El Larguero SER Podcast
- Nadie Sabe Nada SER Podcast
- SER Historia SER Podcast
- Todo Concostrina SER Podcast
- 安住紳一郎の日曜天国 TBS RADIO
- アンガールズのジャンピン[オールナイトニッポンPODCAST] ニッポン放送
- 辛坊治郎 ズーム そこまで言うか! ニッポン放送
- 飯田浩司のOK! Cozy up! Podcast ニッポン放送
- 吳淡如人生實用商學院 吳淡如
- 武田鉄矢・今朝の三枚おろし 文化放送PodcastQR
Otros podcasts de Noticias y Politica
- The Ray Hadley Morning Show 2GB
- Ben Fordham Live on 2GB Breakfast Radio 2GB
- The Bolt Report Sky News Australia / NZ
- You Cannot Be Serious Sam Newman
- Nights with John Stanley 2GB & 4BC
- Dateline NBC NBC News
- Credlin Sky News Australia / NZ
- Global News Podcast BBC World Service
- 3AW Mornings with Tom Elliott 3AW
- Late Night Live - Full program podcast ABC listen
- The Dan Bongino Show Cumulus Podcast Network | Dan Bongino
- Paul Murray Live Sky News Australia / NZ
- The Rita Panahi Show Sky News Australia / NZ
- Six Tackles With Gus 9Podcasts
- Ukraine: The Latest The Telegraph
- Sky Sports Radio's Big Sports Breakfast Sky Sports Radio
- Australia Overnight with Mike Jeffreys 2GB
- The Sean Hannity Show Sean Hannity
- 2GB Weekends - Full Show 2GB
- UFO WARNING UFO WARNING